የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 12/15 ገጽ 24-25
  • “በይሖዋ ፊት ውድ ነኝ!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በይሖዋ ፊት ውድ ነኝ!”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ውድ አድርጎ ይመለከትሃል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • በአምላክ ፊት ውድ ናችሁ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • “ከአምላክ ፍቅር ሊለየን” የሚችል ነገር የለም
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ለእውነት የቆሙ ወቅታዊ መጽሔቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 12/15 ገጽ 24-25

“በይሖዋ ፊት ውድ ነኝ!”

በዚህ “የሚያስጨንቅ ዘመን” ውስጥ ብዙ ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ከሚሰማቸው የከንቱነት ስሜት ጋር የማያቋርጥ ትግል አለባቸው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1) ሰይጣን ከሚጠቀምባቸው “የተንኮል ዘዴዎች” አንዱ፣ አንድም የሚወደን ሰው እንደሌለ ሌላው ቀርቶ ፈጣሪያችንም እንኳ እንደማይወደን እንዲሰማን ማድረግ ስለሆነ ይህ የሚያስደንቅ አይደለም! (ኤፌሶን 6:11 አዓት የግርጌ ማስታወሻ) ከዚህ ጋር በሚስማማ መንገድ የሚያዝያ 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ እትም “በአምላክ ፊት ውድ ናቸሁ!” እና “ለፍቅርና ለመልካም ሥራ ማነቃቃት ያለባችሁ እንዴት ነው?” የተሰኙ በጉባኤ የሚጠኑ ሁለት ርዕሶችን አውጥቶ ነበር። እነዚህ ርዕሶች የወጡት ይሖዋ ጥረቶቻችንን ከፍ አድርጎ እንደሚመለከታቸው ለማስታወስ ነው። የሚከተሉት ሐሳቦች ለዚህ ትምህርት ከተሰጡት የአድናቆት አስተያየቶች ጥቂቶቹ ናቸው፦

“የይሖዋ ምሥክር ሆኜ ባሳለፍኳቸው 27 ዓመታት ውስጥ እንደዚህ የነካኝ መጽሔት የለም። እንባዬን ልቆጣጠረው አልቻልኩም፤ እነዚህ ርዕሶች ይህ ነው የማይባል እፎይታ አምጥተውልኛል። በአሁኑ ጊዜ ይሖዋ በጣም እንደሚወደኝ ይሰማኛል። ሁኔታው ከትከሻዬ ላይ ከባድ ሸክም የወረደልኝ ያህል ነው።”—ሽ ኤች

“ይህን መጽሔት በአንድ ቀን አራት ጊዜ አነበብኩት። ምንም ዋጋ እንደ ሌላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችኋል ሲል ይህ ርዕስ የተጠቀመበት አገላለጽ በጣም አስደስቶኛል። የእረኝነት ጉብኝት ሳደርግና ከቤት ወደ ቤት ሳገለግል ይህን ሐሳብ ልጠቀምበት አስቤአለሁ።”—ኤም ፒ

“ሰይጣን ይሖዋን የሚወዱ ሰዎች እንኳ ምንም ዋጋ እንደሌላቸውና ማንም እንደማይወዳቸው እንዲሰማቸው በማድረግ ረገድ በእጅጉ ተሳክቶለታል። ‘የታማኝና ልባም ባሪያ’ ክፍል ይሖዋ ለእኛ ጥልቅ ፍቅር እንዳለውና መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም እንኳ ለእሱ የምናደርገውን ነገር እንደሚያደንቅ ማስታወሱ እስካሁን ካነበብኳቸው በጣም የሚያበረታቱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። በእነዚህ ርዕሶች ውስጥ የገለጻችኋቸው ስሜቶች ለብዙ ዓመታት በውስጤ ነበሩ። ይሖዋ ፈጽሞ ፍቅሩን ሊያሳየኝ የሚገባኝ ሰው አይደለሁም የሚል አመለካከት ስላደረብኝ ይህን ፍቅር ለማትረፍ ስል በአገልግሎት የበለጠ ለመሳተፍ ሞከርኩ። ይሁን እንጂ ይህን እንዳደርግ የገፋፋኝ የጥፋተኝነት ስሜትና ሐፍረት ነበር። ስለዚህ በአገልግሎት ብዙ ሰዓት ባሳልፍም ወይም ብዙ ሰዎች ብረዳም እንኳ ይህ በቂ እንዳልሆነ ይሰማኝ ነበር። ሁልጊዜ የሚታየኝ ጉድለቴ ብቻ ነበር። አሁን ግን ይሖዋን በፍቅር ተነሣስቼ ሳገለግለው ሲደሰትና ሲኮራብኝ ይታየኛል። ይህም ለእሱ ያለኝ ፍቅር ይበልጥ እያደገ እንዲሄድና የበለጠ እንድሠራ አነሣስቶኛል። በአሁኑ ወቅት ለይሖዋ ከማቀርበው አገልግሎት ከፍተኛ ደስታ በማግኘት ላይ ነኝ።”—አር ኤም

“እነዚህ እስካሁን ካነበብኳቸው ሁሉ እጅግ የላቁ፣ በጣም የሚያበረታቱና ልባችንን የነኩ ተወዳዳሪ የሌላቸው ርዕሶች ናቸው! ላለፉት 55 ዓመታት መጠበቂያ ግንብ ን ያነበብኩ ስሆን ብዙ የማይረሱ እትሞች ወጥተዋል። ሆኖም ‘ምንም ዋጋ እንደሌለን፣’ ‘ማንም እንደማይወደን’ እና በይሖዋ ‘ለመወደድ’ ማድረግ የምንችለው ነገር እንደሌለ የሚያድሩብንን ጥርጣሬዎች፣ ስጋቶችና ፍርሃቶች በማስወገድ ረገድ ይህ እትም ተወዳዳሪ የለውም። ይህ መጠበቂያ ግንብ ወንድሞቻችን በጣም የሚያስፈልጋቸውን መንፈሳዊ እርዳታ ይዟል። እነዚህን ርዕሶች ዘወትር የእረኝነት ጉብኝት በማደርግበት ጊዜ ልጠቀምባቸው አስቤአለሁ።”—ኤፍ ኬ

“ለራሳችን ካለን አነስተኛ ግምት ጋር ለምንታገልና አልፎ ተርፎም ራሳችንን የመጥላት ስሜት ላደረብን ሰዎች በእውነት ውስጥ ለመቀጠል የሚያስችለንን ኃይል ማግኘት በጣም ያስቸግረናል። ይህ ርዕስ ጥልቅ ርኅራኄና የአሳቢነት መንፈስ የተንጸባረቀበት ነው። ይህ አንድ ቁስል የሚያስከትለውን ሥቃይ የሚያስታግሥ ቅባት በመቀባት እንዲጠገን የማድረግ ያህል ነው። በቀጥታ ልብ ውስጥ ጠልቆ ይገባል። በመጠበቂያ ግንብ ላይ እንደዚህ ያሉ ቃላትን ማንበብና ይሖዋ በእርግጥ የሰውን ችግር እንደሚረዳ ማወቅ ምንኛ ያጽናናል! ይሖዋ ሕዝቡን የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው፣ እንዲሸማቀቁ ወይም እንዲፈሩ በማድረግ ለመገፋፋት እንደማይሞክር ስላስገነዘባችሁን አመሰግናችኋለሁ። በአሁኑ ወቅት በቤተሰቤ ውስጥ ባለው የገንዘብና የጤንነት ችግር ምክንያት ለስብከቱ ሥራ የማደርገው አስተዋጽኦ በጣም አነስተኛ ቢሆንም ላደርገው ከምችለው ነገር እርካታ በማግኘት ላይ ነኝ። የሚያስገድደኝ ኃይል ፍቅር እንዲሆን ለማድረግ ስሞክር ከአገልግሎት ይበልጥ ደስታ እንደማገኝ ተገንዝቤአለሁ።”—ዲ ኤም

“‘በአምላክ ፊት ውድ ናቸሁ!’ የሚለውን ርዕስ ገና አሁን አንብቤ መጨረሴ ነው! እያንዳንዱን አንቀጽ ሳነብ ዓይኖቼ እንባ ያቀርሩ ነበር። ያደግሁት እምብዛም ፍቅር በማያሳይ ቤተሰብ ውስጥ ነው። ብዙውን ጊዜ ሰዎች ያንቋሽሹኝ፣ ያፌዙብኝና ይቀልዱብኝ ነበር። ስለዚህ ገና ከልጅነቴ ምንም ዋጋ እንደሌለኝ ተሰማኝ። አሁንም ቢሆን አንድ ችግር ሲያጋጥመኝ ጭንቀት የሚፈጥሩብኝ ቀደም ሲል የነበሩኝ ስሜቶች አሉ። የጉባኤ ሽማግሌ ሆኜ ማገልገሌን ሳቆም እንደ ወትሮው ለአምላክ፣ ለቤተሰቤና በጉባኤ ውስጥ ላሉ ወንድሞች ማድረግ የሚገባኝን እንዳላደረግሁ ተሰምቶኝ ነበር። እነዚህ ስሜቶች ወዲያውኑ ባይጠፉም ይህ ርዕስ በተወሰነ ደረጃ ሚዛኔን እንድጠብቅ ረድቶኛል። ብሩህ አመለካከት እንድይዝ አድርጎኛል።”—ዲ ኤል

“‘በአምላክ ፊት ውድ ናቸሁ!’ በሚል ርዕስ ላቀረባችሁት ትምህርት አመሰግናችኋለሁ። በልጅነቴ በተፈጸመብኝ የጾታ መነወር ምክንያት ለራሴ ካደረብኝ ከባድ ጥላቻና ጥልቅ የሆነ የዋጋ ቢስነት ስሜት ጋር እየታገልኩ ነው። ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ የሰይጣን የተንኮል ዘዴ እንደሆነ አድርጎ መመልከት ፍጹም ተገቢ ነው። እንዲያውም ይህ ስሜት አንድ ሰው ለመኖር ያለውን ፍላጎት ሊያጠፋበት ይችላል። በእርግጥም እኔን የሚወደኝ የለም የሚለውን አስተሳሰብ ለመቃወም በየቀኑ መታገል ይኖርብኛል። ይህ ርዕስ እናንተ ልትገምቱት ከምትችሉት በላይ ጠቅሞኛል።—ኬ ኤፍ

“ዛሬ ወንድሞች በተለይ ይሖዋ በግዴታ ወይም በግፊት ሳይሆን በፍቅር ተነሣስቶ ለሚደረጉ ሥራዎች ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ ለሚናገረው ትምህርት አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል። ይሖዋ ያለውን ሞቅ ያለ የወዳጅነት ስሜት፣ ተወዳጅ ስብዕናውን፣ ለሕዝቦቹ በግለሰብ ደረጃ የሚያሳየውን አሳቢነት እና ራሱን ያቀረበበትን ፍቅራዊ መንገድ ማሰባችን ሕይወትን የሚያድስ ከመሆኑም በላይ የሚገፋፋ ስሜት ያሳድርብናል። በዚህ ረገድ ‘በአምላክ ፊት ውድ ናቸሁ!’ በሚል ርዕስ የቀረበውን ትምህርት በተመለከተ ብዙዎች ወዲያውኑ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ብዙ ሰዎች ከይሖዋ ጋር ያላቸውን የግል ዝምድና የበለጠ የሚያጠናክሩበት መንገድ የተከፈተላቸው ይመስላል። እኔና ባለቤቴ በቅርብ ጊዜያት የወጡት የመጠበቂያ ግንብ መጽሔቶች አቀራረብና የሌሎችን ስሜት ከግምት ውስጥ ማስገባታቸው እንዳስደሰተን ለመግለጽ እንፈልጋለን። ጉባኤዎችን በምንጎበኝበት ወቅት ከእነዚህ ነጥቦች ብዙዎቹን ለመጠቀም በመጣር ላይ ነን።”—አንድ ተጓዥ የበላይ ተመልካች

“ላለፉት ወደ 30 የሚጠጉ ዓመታት ዘወትር አነብ የነበርኩ ብሆንም እንደዚህ ያለ መንፈስን የሚያነሣሣና የሚያበረታታ ነገር አላነበብኩም። ኃይለኛ የሆኑትና በጥበብ የተመረጡት ጥቅሶች ከስሜቶቼ በስተጀርባ የተደበቁትን ውሸቶች እንድገነዘብ ስለረዱኝ ወደ ይሖዋ የበለጠ ለመቅረብ ችያለሁ። ለብዙ ዓመታት ይሖዋን ሳመልከው የነበረው በጥፋተኝነት ስሜት ተነሣስቼ ነበር። ቤዛውንና የአምላክን ፍቅር በተመለከተ የነበረኝ እውቀት የጭንቅላት እውቀት ብቻ ነበር። ለእነዚህ ጥልቀት ያላቸውና አሳቢነት የታከለባቸው ርዕሶች አመሰግናችኋለሁ። እንደነዚህ ያሉ ብዙ ትምህርቶችን ለማንበብ ተስፋ አደርጋለሁ።”—ኤም ኤስ

“በእውነት በቆየሁባቸው 29 ዓመታት ውስጥ እንዲህ ያለ አድናቆትና ጥልቅ ስሜት ያሳደረብኝን ርዕስ አላስታውስም። ምንም እንኳ ከፍተኛ ፍቅርና እንክብካቤ በሚደረግበት ቤተሰብ ውስጥ ያደኩ ብሆንም ይሖዋን ለማገለገል ይቅርና በሕይወት ለመቆየት እንኳ ይገባኛል ብዬ አስቤ አላውቅም። ይህን ርዕስ ካነበብኩ በኋላ በጉልበቴ ተንበረከኩና ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ ይሖዋን አመሰገንኩት። ይህን ርዕስ እንደ ውድ ሀብት አድርጌ ለዘላለም እመለከተዋለሁ። አሁን በይሖዋ ፊት ውድ እንደ ሆንኩ ስለተገነዘብኩ ለራሴ ያለኝ አመለካከት ተለውጧል።”—ዲ ቢ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ