የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 9/15 ገጽ 32
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 9/15 ገጽ 32

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ

በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ በኢምፔሪያል ዎር ሙዚየም ውስጥ ለሕዝብ የሚታይ አንድ ልዩ የግድግዳ ሰዓትና አንድ ኤሌክትሮኒክ አሃዛዊ ቆጣሪ አለ። ሰዓት አመልካቹ ቀስት በዞረ ቁጥር ቆጣሪው በየ3.31 ሴኮንድ ልዩነት አንድ ጊዜ ድምፅ ያሰማል። ይህ አሃዛዊ ቆጣሪ ድምፅ ባሰማ ቁጥር አስቀድሞ በመዘገበው ጠቅላላ ቁጥር ላይ ሌላ ተጨማሪ ቁጥር ይደምራል። የሚያሰማው እያንዳንዱ ድምፅና እያንዳንዱ ቁጥር በዚህ መቶ ዘመን በሚደረገው ጦርነት ምክንያት የሚሞተውን አንድ ወንድ፣ አንዲት ሴት ወይም ሕፃን ያመለክታል።

ቆጣሪው ምዝገባውን የጀመረው ሰኔ 1989 ሲሆን በ2000 ዓመት ዋዜማ እኩለ ሌሊት ላይ ቆጠራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። በዚያን ጊዜ በቆጣሪው ላይ የሚነበበው አሃዝ አንድ መቶ ሚልዮን ይሆናል። ይህም በ20ኛው መቶ ዘመን ከጦርነት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የሞቱትን ሰዎች የሚገልጽ ግምታዊ ቁጥር ነው።

የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ ኢየሱስ ክርስቶስ ‘ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ የሚነሳበት’ ዘመን እንደሚመጣ ተንብዮ ነበር። በዚህም መሠረት ለቁጥር የሚያታክቱት የምድር መንቀጥቀጦች፣ ወረርሽኞች፣ የምግብ እጥረትና ሌሎች ክስተቶችን ጨምሮ በዚህ መቶ ዘመን የደረሱት አውዳሚ ጦርነቶች አንድ ላይ ተዳምረው ኢየሱስ በ1914 በሰማይ ንጉሥ ከሆነ በኋላ ባሉት ጊዜያት ማለትም ‘በመጨረሻው ዘመን’ እንደምንኖር የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች መሆናቸውን የይሖዋ ምሥክሮች ከረዥም ጊዜ ጀምረው ሲሰብኩ ቆይተዋል።—ሉቃስ 21:10, 11፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:1

መጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መጨረሻው ባለ ሥልጣን አድርጎ በመጠቀም የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ጨቋኞችን አጥፍቶ ምድርን ወደ ገነትነት እንደሚለውጥ የሚገልጸውን ምሥራች ያውጃል። ታዲያ ጦርነት ወደፊት ምን ይሆናል? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦ “የእግዚአብሔርን ሥራ፣ በምድር ያደረገውንም ተአምራት እንድታዩ ኑ። እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ይሽራል፤ ቀስትን ይሰብራል፣ ጦርንም ይቆርጣል፣ በእሳትም ጋሻን [“የጦር ሰረገሎችንም፣” አዓት] ያቃጥላል።”—መዝሙር 46:8, 9

[ምንጭ]

ሰዓት፦ By Courtesy of the Imperial War Museum

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ