የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 8/15 ገጽ 32
  • የናዚን ስደት በጽናት ተቋቁመዋል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የናዚን ስደት በጽናት ተቋቁመዋል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 8/15 ገጽ 32

የናዚን ስደት በጽናት ተቋቁመዋል

የይሖዋ ምሥክሮች በናዚ ጀርመን ያሳዩት ድፍረት የተሞላበት የጸና አቋም የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት ከወሰዱት አቋም ጋር ሲነጻጸር ጉልህ የሆነ ልዩነት አለው። ይህ ጉዳይ የታሪክ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ጆን ዋይስ አይዲኦሎጂ ኦቭ ዴዝ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ሰፍሮ ይገኛል። እንዲህ በማለት ጽፈዋል:-

“በ1934 የኢቫንጄሊካል ቤተ ክርስቲያን ‘ሉተራውያን ናዚን በደስታ መቀበል አለባቸው’ በማለት አደፋፍረዋቸዋል። እንዲሁም ‘ጌታ አምላክ’ ‘ጻድቅና እምነት የሚጣልበት ጌታ’ ለጀርመን በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል። . . . አንድ የፕሮቴስታንት ጳጳስ ‘አምላክ [ሂትለርን] ለእኛ ልኮልናል’” በማለት ለቄሱ ጽፈዋል። ዋይስ በመቀጠል:- “ሂትለር ሰላምንና መረጋጋትን በማምጣት ከቦልሼቪክ አብዮት ጀርመንን አድኗል . . . በሚለው አባባል የጀርመኑ ሜቶዲስት ቤተ ክርስቲያን ከጳጳሱ ዴቤልየስ ጋር ተስማምቷል። . . . የሞርሞን ቤተ ክርስቲያን ሂትለርን መቃወም የሞርሞንን ሕግ መጣስ እንደሆነ ለአባላቱ አስታውቋል” ሲሉ ጽፈዋል። እንዲህ በማለትም አክለዋል:- “አዲሱን መንግሥት መታዘዝ የተቀደሰ ተግባር እንደሆነና በምሥራቅ ከፍተኛ ሰቆቃ እንደደረሰ ቀሳውስቱ ቢያውቁም እንኳ ይህ ተግባር ፈጽሞ የማይቀር እንደሆነ ለካቶሊኮች ተነግሯቸዋል።”

ይሁን እንጂ የይሖዋ ምሥክሮችን በተመለከተ ምን ለማለት ይቻላል? ፕሮፌሰር ዋይስ “በቡድን ደረጃ ናዚን ፊት ለፊት የተጋፈጡት የይሖዋ ምሥክሮች ብቻ ናቸው።” በሺህ የሚቆጠሩ የታሰሩ ነበሩ፤ ፐሮፌሰር ዋይስ በመቀጠል “ሆኖም ወደ ማጎሪያ ካምፕ የተላኩት ምሥክሮች ሁሉ እምነታቸውን እንደተዉ በሚያረጋግጠው ሰነድ ላይ ቢፈርሙ ኖሮ ይለቀቁ ነበር” በማለት አመልክተዋል።

የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩትን ጽኑ አቋም በማስመልከት ፕሮፌሰር ዋይስ ሐሳብ ሲሰጡ “ያሳዩት ምሳሌ የጥንቱ ክርስትና ሥር ከመስደዱና በኅብረተሰቡ ዘንድ እውቅና ከማትረፉ በፊት ይዞ ከነበረው የጸና አቋም፣ በዓይነቱ ልዩ ከሆነው ቆራጥነትና ጀግንነት ጋር አንድ ዓይነት ነው። አንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር እነርሱን በማስመልከት ‘በንዴት የጦፈውን የናዚን አገዛዝ በአንደኛ ደረጃ የተጋፈጡትና ከእምነታቸው ጋር በመስማማት በድፍረት የተቃወሙት በሰፊው የታወቁት አብያተ ክርስቲያናት ሳይሆኑ በሰዎች ዘንድ የስድብና የፌዝ ዒላማ የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው’” በማለት ጽፈዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ