የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 11/15 ገጽ 32
  • እንቅልፍ ማጣት ያስገኘው ጥቅም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንቅልፍ ማጣት ያስገኘው ጥቅም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 11/15 ገጽ 32

እንቅልፍ ማጣት ያስገኘው ጥቅም

ነገሥታት እንኳን ሳይቀር እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር የሚያድሩባቸው ሌሊቶች አሉ። በአምስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ይኖር የነበረው የፋርሱ ኃያል ገዥ አርጤክስስ እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሞት ነበር። አንዳንድ የዘነጋኋቸው ተግባራት ይኖሩ ይሆናል ብሎ በማሰብ የቤተ መንግሥቱን የታሪክ መዝገብ አምጥተው እንዲያነቡለት አደረገ። መርዶክዮስ የሚባል አንድ ታማኝ አገልጋይ ንጉሡን ለመግደል የተጠነሰሰውን ሴራ ቢያጋልጥም ምንም ካሣ እንዳልተከፈለው ተገነዘበ። አርጤክስስ ይህን ስሕተት ለማረም ወዲያውኑ እርምጃ ወሰደ። የወሰደው እርምጃ ለአምላክ ሕዝቦች ያስገኘው መልካም ውጤት ንጉሡ እንቅልፍ እንዲያጣ የተደረገው በመለኮታዊ ኃይል መሆኑን ያሳያል።​—⁠አስቴር 6:​1-10

በደቡብ አፍሪካ በባህር ዳርቻ በሚገኝ ኸርማንስ በሚባል ከተማ ያለ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዲያስታውስ የሚያደርግ ሁኔታ አጋጥሞታል። ወንድሞች የሚሰበሰቡት በተከራዩት አዳራሽ ውስጥ ነበር። የራሳቸው የሆነ የመንግሥት አዳራሽ ለመሥራት የሚያስችል መሬት ለመግዛት ለብዙ ዓመታት ጥረዋል። በመጨረሻም የከተማው ምክር ቤት በ1991 ግሩም የሆነ ቦታ ሰጣቸው።

ይሁን እንጂ አንዳንዶች ቦታው ለይሖዋ ምሥክሮች መሸጡን ተቃወሙ። ጉዳዩ ለበርካታ ወራት ሲጓተት ከቆየ በኋላ ምክር ቤቱ ለቤተ ክርስቲያኖች መሬት እንዳይሸጥ የሚከለክል ለሦስት ዓመታት የሚቆይ እገዳ መጣሉን ለጉባኤው በመንገር ወንድሞች የተመሩትን መሬት እንዳይወስዱ ከለከለ። በግንቦት ወር 1993 ጉባኤው በድጋሚ በመጻፍ ምክር ቤቱ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደገና እንዲመረምር ጠየቀ። ወንድሞች ያገኙት መልስ እገዳው እንዳልተነሣ የሚገልጽ አንድ ዓረፍተ ነገር የያዘ ደብዳቤ ነበር።

በዚያው ዓመት በጥቅምት ወር ከምክር ቤቱ አባላት ውስጥ አንዷ አንድ ቀን ሌሊት እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር ያድራሉ። ትኩረት የሚሹ ነገሮች መኖራቸውን ለማየት ሲሉ የምክር ቤቱን የቆዩ መዝገቦች በማገላበጥ ጊዜውን አሳለፉ። መዝገቦቹን እያገላበጡ ሳለ ምክር ቤቱ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደገና እንዲያጤን ለመጠየቅ ምሥክሮቹ የጻፉት ደብዳቤ ትኩረታቸውን ይስበዋል። ስለዚህ ጉዳዩን በሚቀጥለው የስብሰባ አጀንዳ ላይ ለማንሳት ወሰኑ። የይሖዋ ምሥክሮች ማመልከቻቸውን ያስገቡት ለቤተ ክርስቲያኖች መሬት መሸጥን የሚከለክለው እገዳ ከመጣሉ በፊት መሆኑን ለመጥቀስ ፈልገው ነበር።

ከጊዜ በኋላ ጉባኤው ቀደም ሲል በ1991 ተመርቶ የነበረውን ያንኑ መሬት እንዲወስድ ተደረገ! ቦታው የሚገኘው በዋናው መንገድ ላይ ስለሆነ ለጉባኤው አባላትም ሆነ ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች አመቺ ነው። ወንድሞች በቦታው ላይ ግሩም የሆነ የመንግሥት አዳራሽ የሠሩ ሲሆን አዳራሹ በጥቅምት 5, 1996 ለይሖዋ አገልግሎት ተወስኗል።

ጉባኤው የምክር ቤቱ አባል እንቅልፍ አጥተው ማደራቸው ቢያሳዝነውም እኚህ ሴት፣ ንጉሥ አርጤክስስ እንኳን ሳይቀር እንቅልፍ በዓይኑ ሳይዞር ያደረበት ጊዜ እንዳለ ቢያውቁ ሊጽናኑ ይችላሉ። ደግሞም በሁለቱም ወቅቶች የተገኘው ውጤት ጠቃሚ ነበር። በኸርማንስ ያለው ጉባኤ በባህር ዳርቻ በሚገኘው በዚህ ደስ የሚል ከተማ ለንጹሕ አምልኮና ለቲኦክራሲያዊ ሥልጠና ማዕከል የሚሆን የራሱ የሆነ የመንግሥት አዳራሽ በማግኘቱ እጅግ ተደስቷል።​—⁠ዕብራውያን 10:​24, 25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ