የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 12/1 ገጽ 32
  • አሥርቱ ትእዛዛት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አሥርቱ ትእዛዛት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 12/1 ገጽ 32

አሥርቱ ትእዛዛት

በእንግሊዝ የግሎስተር ጳጳስ በእርሳቸው ሃገረ ስብከት ውስጥ ካሉት ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ቄሶች አሥርቱን ትእዛዛት በቃላቸው እንደማያውቁና ከእነዚህም መካከል 10 ከመቶ የሚሆኑት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የት ላይ እንደሚገኝ እንደማያውቁ ደርሰውበታል። ይህ የሆነው ከ450 ዓመታት በፊት ነው። ከዚያን ጊዜ በኋላ ሁኔታው ተሻሽሏልን? በቅርቡ ሰንዴይ ታይምስ በአንዳንድ የአንግሊካን ቀሳውስት ላይ ያካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው ሁኔታው በጭራሽ አልተሻሻለም።

ቃለ መጠይቅ ከቀረበላቸው 200 ቀሳውስት መካከል 34 በመቶዎቹ ብቻ አሥርቱን ትእዛዛት በቃላቸው መጥቀስ ችለዋል። ከተቀሩት መካከል ደግሞ አንደኛው ቄስ አሥርቱ ትእዛዛት እገዳዎች እንደሚያበዙ የተሰማቸው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በዘመናችን ላሉት የሥነ ምግባር ችግሮች ተግባራዊ መፍትሄ አይሰጡም በማለት አጣጥለዋቸዋል።

አንተስ አሥርቱ ትእዛዛት የትኞቹ እንደሆኑ ወይም የት ላይ እንደሚገኙ ታውቃለህ? የመጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛ መጽሐፍ በሆነው በዘጸአት መጽሐፍ በ20ኛው ምዕራፍ በመጀመሪያዎቹ 17 ቁጥሮች ላይ ሰፍረው ይገኛሉ። ለምን አታነባቸውም? አሥርቱን ትእዛዛት ከፋፍሎ ለማስቀመጥ የሚረዳ ቀላል ዘዴ እንደሚከተለው ቀርቧል። የመጀመሪያዎቹ አራቱ ለአምላክ የምናቀርበውን አምልኮ ያመለክታሉ፣ አምስተኛው የቤተሰብ ሕይወትን ያጎላል፣ ከቁጥር ስድስት እስከ ዘጠኝ ያሉት ከሌሎች ሰዎች ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ግንኙነት ይገልጻሉ፣ እንዲሁም አሥረኛው ለየት ያለ ሕግ ሲሆን ልባችንን እንድንፈትሽ ማለትም ውስጣዊ ግፊታችንን እንድንመረምር ይገፋፋናል። ክርስቲያኖች መሠረታዊ ሥርዓቶቹን እንዴት በሥራ ላይ ሊያውሉ እንደሚችሉ ለማሳየት ከዚህ ቀጥሎ ፍሬ ነገሩ ባጭሩ ቀርቧል።

አንደኛ:- ለፈጣሪያችን ብቻ የተወሰነ አምልኮ አቅርብ። ሁለተኛ:- ለአምልኮ ምስሎችን አትጠቀም። ሦስተኛ:- በሐሳብም ሆነ በድርጊት ዘወትር የአምላክን ስም አክብር። አራተኛ:- በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ብቻ የምታተኩርበት ጊዜ መድብ። አምስተኛ:- ልጆች ወላጆቻችሁን አክብሩ። ስድስተኛ:- አትግደል። ሰባተኛ:- ከዝሙት ሽሽ። ስምንተኛ:- አትስረቅ። ዘጠነኛ:- አትዋሽ። አሥረኛ:- ከመመኘት ራቅ።

አሥርቱ ትእዛዛት ለሙሴ ከተሰጡት ሕጎች ውስጥ ይካተቱ ነበር። ሆኖም የያዟቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች ጊዜ አይሽራቸውም። (ሮሜ 6:​14፤ ቆላስይስ 2:​13, 14) በዚህም ምክንያት የኢየሱስ ተከታዮች ከአሥርቱ ትእዛዛት ጠቅሰው ከመናገራቸውም በላይ ሰዎች እንዲመለከቷቸው ጠቁመዋል። (ሮሜ 13:​8-10) ሁሉም ሰዎች እነዚህን በመለኮታዊ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ መሠረታዊ ሥርዓቶች ቢያከብሩና ሕይወታቸውን ቢመሩባቸው በዛሬው ጊዜ ሕይወት እንዴት አስደሳችና አስተማማኝ ይሆን ነበር!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ