የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 1/1 ገጽ 32
  • አፍ የሚያስይዝ መልስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አፍ የሚያስይዝ መልስ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 1/1 ገጽ 32

አፍ የሚያስይዝ መልስ

በእንግሊዝ አገር የሚገኘው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚያሳትመው ካቶሊክ ሄራልድ የተባለው ጋዜጣ በቅርቡ ዌልስ ከሚገኝ አንድ አንባቢ የተላከለትን ቀጥሎ የቀረበውን ደብዳቤ አትሞ አውጥቷል:- “አንድ ቀን ምሽት ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቴ መጡ። እነርሱ የጠቀሱትን አዲስ ኪዳን ትክክለኛነት ያረጋገጠው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ነገርኳቸው። አንደኛው በዚህ አባባል እንደሚስማማ ሲገልጽልኝ በጣም ተደነቅሁ። ‘እርግጥ ትክክለኛነቱን አረጋግጣችኋል፤ ሆኖም አትመሩበትም’ ብሎ መለሰልኝ። ‘ኢየሱስ “እኔ እንደወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” ብሏል፤ እናንተ ግን እርስ በርስ ትገዳደላላችሁ። ከዚህ ቀደም በተደረገው ጦርነት ካቶሊኮች ካቶሊኮችን ገድለዋል ነገር ግን የትኛውም የይሖዋ ምሥክር የእምነት ጓደኛውን አልገደለም።’ ምንም መልስ አልነበረኝም። በእኛ መካከል እውነተኛ አንድነት ሳይኖር እንዴት ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው መጸለይ እንችላለን? በመጀመሪያ ይህን አሳፋሪ ድርጊት ማረም አይገባንምን?”​—⁠ዮሐንስ 15:​12

በዚህ 20ኛው መቶ ዘመን የተደረጉት ሁለቱ የዓለም ጦርነቶች የተቆሰቆሱት በሕዝበ ክርስትና ውስጥ ሲሆን ከ50 እስከ 60 ሚልዮን የሚያህል ሕይወት ቀጥፈዋል። ሆኖም የይሖዋ ምሥክሮች በእነዚህ ጦርነቶች ተሳትፎ እንዳላደረጉና ባሁኑ ጊዜም እየተካሄዱ ባሉት ግጭቶች ተካፋይ እንዳልሆኑ በሐቀኝነት መናገር ይቻላል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት ሚልዮን በላይ የሆኑትን የይሖዋ ምሥክሮች ስላስተሳሰሩት የክርስቲያናዊ ፍቅርና አንድነት ጠንካራ ማሰሪያዎች ይበልጥ ለማወቅ ብትጥር ትጠቀማለህ።​—⁠ከኢሳይያስ 2:​4 ጋር አወዳድር።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

U.S. National Archives photo

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ