አንድ “በዓይነቱ ልዩ የሆነ” ትልቅ ስብሰባ ተደነቀ
በፔሩ፣ ሊማ የሚገኝ አንድ የራዲዮ ፕሮግራም አስተዋዋቂ የይሖዋ ምሥክሮችን በጥርጣሬ ዓይን ይመለከት ነበር። ሆኖም በአንድ የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ከተገኘ በኋላ አመለካከቱ በሚያስደንቅ ሁኔታ ተለወጠ። እንዲያውም በነገሩ በጣም ተነክቶ ስለነበር ለራዲዮ አድማጮቹ አንዳንድ ገንቢ አስተያየቶች ሰንዝሯል። የሚከተለው ሐሳብ እርሱ ከተናገረው ውስጥ በከፊል የተወሰደ ነው:-
“ቃል በቃል ለመናገር ስብሰባው በዓይነቱ ልዩ የሆነ ነበር። በአካባቢው ሱቅ በደረቴም ሆነ መሬት ላይ የወደቀ አንድም ቁራጭ ወረቀት አልነበረም። መተላለፊያዎች በሰው አልተጨናነቁም ነበር። አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰዎች ቦታውን ለማጠብና ለመጥረግ እያንዳንዳቸው ባልዲ፣ መወልወያ፣ አቧራ መጥረጊያ፣ የቆሻሻ ማፈሻ፣ መጥረጊያ፣ የእጅ ብሩሽ፣ ጓንት፣ ኦሞና ሌሎች ማጽጃ ኬሚካሎች ይዘው በራሳቸው ወጪ ወደ ስታዲየሙ መጡ። ቀለም መቀባት የሚያስፈልገውን ሁሉ ቀለም ቀቡት። ገንዘቡ ከየት ተገኘ? ራሳቸው ያዋጡት ነው! አንድ መሠራት ያለበት ነገር እንዳለ ሲነገራቸው ሁሉም ገንዘብ ለመስጠት ዝግጁዎች ናቸው። እውነቴን ነው የምላችሁ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደነዚህ ለመሳሰሉት ጉዳዮች ትኩረት አትሰጥም። የይሖዋ ምሥክሮችንና የዚህን ፕሮግራም አስተባባሪዎች ለማመስገን እፈልጋለሁ። በተጨማሪም አምላክ ይርዳችሁ እንዲሁም ይባርካችሁ ብዬ ልባዊ ምኞቴን ለእነርሱ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።”
በዚህ ዓመት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከተማዎች የይሖዋ ምሥክሮች “አምላካዊ አኗኗር” የተባለውን የአውራጃ ስብሰባ ያደርጋሉ። አንተስ በዚያ ትገኛለህ?
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
“መሬት ላይ የወደቀ አንድም ቁራጭ ወረቀት አልነበረም”