የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 7/15 ገጽ 32
  • “የአንድነትና የወንድማማችነት ምሳሌ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የአንድነትና የወንድማማችነት ምሳሌ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 7/15 ገጽ 32

“የአንድነትና የወንድማማችነት ምሳሌ”

አንዲት ሴት የቤተሰቧ አባል የሆነ አንድ ሰው በሞተ ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች ያደረጉትን ነገር የገለጸችው በዚህ መልኩ ነበር። እንዲህ ስትል ተናግራለች:-

“በፍራይቡርግ ጀርመን የሚገኘውን የጣሊያንኛ ጉባኤ ምሥክሮችን በቤተሰቦቼና በራሴ ስም ላመሰግን እወዳለሁ። ከታላቅ ወንድሜ ከአንቶንዮ እና ከባለቤቱ ከአና በስተቀር የተቀረነው የቤተሰባችን አባላት የይሖዋ ምሥክሮች አይደለንም። ምንም እንኳ የሚከተሉትን ሃይማኖት ዘወትር የምናከብርላቸው ቢሆንም የዚህ ሃይማኖት አባል በመሆናቸው ለረዥም ጊዜ ስንተቻቸው ቆይተናል።

“ይሁን እንጂ አሁን አመለካከታችንን ለመቀየር ተገደናል። እውነቱን ለመናገር ያህል ከዚህ ቀደም ፈጽሞ ጠብቀነው የማናውቀውን የወንድማማችነትና የፍቅር ምሳሌ ተመልክተናል።

“የሚያሳዝነው አና በመኪና አደጋ በድንገት ሞተች። የምንኖረው በኢጣሊያ በመሆኑ ወንድሜን አንቶኒዮንና ልጆቹን ብዙ ማጽናናት አልቻልንም። ሆኖም የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑት ወንድሞቹ አስፈላጊውን ድጋፍ አደረጉለት። በአካል በመገኘት፣ በቃል፣ በእምነት፣ በጉልበት፣ በሞራልና በኢኮኖሚ ድጋፍ በመስጠት ረድተውታል። ጉባኤውን በቀጥታ ማመስገን ስለማልችል ላሳዩት ፈጽሞ የማይረሳ የአንድነትና የወንድማማችነት ምሳሌ በመጽሔታችሁ በኩል ላመሰግናቸው እወዳለሁ።”

ይህች ሴት የሰጠችው መልካም አስተያየት የሚደነቅ ነው። እርሷ እንደተመለከተችው የይሖዋ ምሥክሮች ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር ናቸው። (1 ጴጥሮስ 2:​17) ፍቅር “ፍጹም የአንድነት ማሰሪያ” መሆኑን በማወቅ በመካከላቸው ጠንካራ ፍቅራዊ ትስስር አዳብረዋል። (ቆላስይስ 3:​14 NW) በሁላችንም ላይ ሊደርስ የሚችል አንድ ዓይነት አሳዛኝ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ እንኳ የይሖዋ ምሥክሮች ከአምላክና ከሕዝቦቹ ጎን ይቆማሉ።​—⁠ምሳሌ 18:​24፤ መክብብ 9:​11፤ ዮሐንስ 13:​34, 35

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ