የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 2/1 ገጽ 24
  • ራቅ ብላ የምትገኝ ትንሽ ደሴት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ራቅ ብላ የምትገኝ ትንሽ ደሴት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 2/1 ገጽ 24

ራቅ ብላ የምትገኝ ትንሽ ደሴት

የሴይንት ሄለናን ደሴት ለመግለጽ አብዛኛውን ጊዜ “ሩቅ” እና “ትንሽ” የሚሉት ቅጽሎች ይገባሉ። ለደሴቲቱ ቅርብ ከሆነው የደቡብ ምዕራባዊ አፍሪካ የባሕር ዳርቻ 1,950 ኪሎ ሜትር ርቃ ለምትገኘው፣ 17 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 10 ኪሎ ሜትር ስፋት ላላት ለዚህች ደሴት የተሰጡት ቅጽሎች ተስማሚ ናቸው። ናፖሊዮን ቦናፓርት በ1815 ምርኮኛ ሆኖ ቀሪ የሕይወት ዘመኑን በግዞት እንዲያሳልፍ የተላከው ወደዚች ደሴት ነበር።

ደሴቲቱን ከውቅያኖሱ ሆኖ ለሚያያት የማይደፈር ምሽግ ትመስላለች። በእርግጥም ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ቀጥ ብሎ የወጣ ከ500 እስከ 700 ሜትር የሚደርስ ዥው ያለ ገደል የሠራ ጥፍ ገሞራ (extinct volcano) አለ። በደሴቲቱ እምብርት ላይ 818 ሜትር ከፍታ ያለው የአክቲየን ተራራ ጉብ ብሎ ይገኛል። ከደቡብ አትላንቲክ በሚነፍሰው ቀዝቀዝ ያለ ነፋስና ቀላይ ሞገድ (ocean current) የተነሳ ደሴቲቱ በአብዛኛው መካከለኛና ተስማሚ የሆነ የአየር ጠባይ አላት። ሆኖም ዝቅተኛ ከሆነው የባሕር ዳርቻ አንስቶ እስከ ውስጠኛው ተራራማ አካባቢ ድረስ የተለያየ ዓይነት የአየር ጠባይና ልዩ ልዩ ዕጽዋት ይገኛሉ።

ሴይንት ሄለና ከ17ኛው መቶ ዘመን ማብቂያ አንስቶ የእንግሊዝ ግዛት ሆና ቆይታለች። ወደ 5,000 የሚጠጋው አነስተኛ ቁጥር ያለው ሕዝቧ የአውሮፓ፣ የእስያና የአፍሪካ ዝርያ ድብልቅ ነው። የመላ ደሴቲቱ የመግባቢያ ቋንቋ እንግሊዝኛ ቢሆንም እንኳ የአነጋገር ዘይቤው ለየት ያለ ነው። በደሴቲቱ ላይ የአውሮፕላን ማረፊያ የለም፤ ከተቀረው የዓለም ክፍል ጋር ግንኙነት የሚደረገው ወደ ደቡብ አፍሪካና እንግሊዝ በሚደረገው ቋሚ የመርከብ ጉዞ አማካኝነት ብቻ ነው። እንዲያውም የቴሌቪዥን ስርጭት መተላለፍ የጀመረው በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ የሳተላይት መስመር በመዘርጋቱ ምክንያት ነው።

በ1930ዎቹ መጀመሪያ ላይ የአምላክ መንግሥት ምሥራች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህች ደሴት ደረሰ። (ማቴዎስ 24:​14) ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ ብዙ የደሴቲቱ ነዋሪዎች ከቁሳዊ ብልጽግና እጅግ የሚልቀውን ይህን ውድ ሀብት አጥብቀው መያዝ ጀመሩ። (ማቴዎስ 6:​19, 20) ዛሬ በሴይንት ሄለና አንድ የይሖዋ ምሥክር በአማካይ ለ31 ሰዎች የሚደርስ ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ሬሾ ሁሉ የተሻለው ነው!

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ሴይንት ሄለና

ጄምስታውን

ሌቭልዉድ

አፍሪካ

አትላንቲክ ውቅያኖስ

ሴይንት ሄለና

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ