ሊታወስ የሚገባው ዕለት
ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ለሐዋርያቱ ያልቦካ ቂጣና ወይን ከሰጣቸው በኋላ እንዲበሉትና እንዲጠጡት አዘዛቸው። በተጨማሪም “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው።—ሉቃስ 22:19
በዚህ ዓመት በዓሉ ሐሙስ፣ መጋቢት 23 (በአውሮፓውያን አቆጣጠር ደግሞ ሚያዝያ 1) ቀን ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይውላል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ልዩ ምሽት ኢየሱስ ባዘዘው መሠረት የመታሰቢያውን በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ። አብረውን እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልዎታለን። እባክዎ ይህ ልዩ ስብሰባ የሚደረግበትን ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ለማወቅ በአካባቢዎ የሚገኙትን የይሖዋ ምሥክሮች ይጠይቁ።