የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 6/1 ገጽ 8
  • የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ላደረገልኝ ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስጋኝ ነኝ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • እንደምትወጂያቸው ንገሪያቸው
    የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች
  • “ይሖዋ እንደገና አገኘኸኝ!”
    ንቁ!—2004
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 6/1 ገጽ 8

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

‘በአምላክ ዘንድ ሁሉ ይቻላል’

በቬነዙዌላ የምትኖር አንዲት ወጣት በማቴዎስ 19:​26 ላይ የሚገኙት ከላይ የተጠቀሱት ቃላት እውነት መሆናቸውን አረጋግጣለች። በይሖዋ ላይ ሙሉ ትምክህት መጣልን ከተማረች በኋላ አንድ ከባድ ችግር ማሸነፍ ችላለች። እንዲህ ትላለች:-

“አያቴ በጣም ደግና አፍቃሪ ነበረች። የሚያሳዝነው ግን ገና የ16 ዓመት ልጅ ሳለሁ ሞተች። የእርሷ ሞት ክፉኛ ጎዳኝ። ሌላው ቀርቶ ወደ ግቢ መውጣት እስኪያስጠላኝ ድረስ ከልክ በላይ በሐዘን ተዋጥኩ። ከዚያም ከሰው መቀላቀል ጨርሶ አስጠላኝ።

“ወደ ትምህርት ቤት አልሄድ፣ ሥራም አልሠራም ነበር። እዚያው ክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብዬ እውል ነበር። አንድም ጓደኛ ስላልነበረኝ ከብቸኝነቴ የተነሳ ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ያዘኝ። ፈጽሞ የማልረባ እንደሆንኩ ስለተሰማኝ ራሴን ገድዬ ለመገላገል ፈለግሁ። ‘ለምን ተፈጠርሁ?’ እያልኩ ደጋግሜ ራሴን እጠይቅ ነበር።

“ጊሴላ የምትባል አንዲት ወጣት የይሖዋ ምሥክር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ለእናቴ ትሰጣት ነበር። አንድ ቀን ጊሴላ በቤታችን አጠገብ ስታልፍ እናቴ አገኘቻትና እኔን መርዳት ትችል እንደሆነ ጠየቀቻት። ጊሴላ ጥረት ለማድረግ ብትስማማም እኔ ግን ከእርስዋ ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ ሳልሆን ቀረሁ። እንዲህ ማድረጌ ጊሴላን ተስፋ አላስቆረጣትም። ደብዳቤ ጽፋ የእኔ ጓደኛ መሆን እንደምትፈልግ፤ እንዲያውም ከእርሷ ይበልጥ የላቀ ቦታ ያለው አንድ አካል ከእኔ ጋር ጓደኛ መሆን እንደሚፈልግ ገለጸችልኝ። ይህም አካል ይሖዋ አምላክ እንደሆነ ነገረችኝ።

“ይህ ልቤን ስለነካው ለደብዳቤዋ መልስ ጻፍኩላት። ለሦስት ወራት ያህል ደብዳቤ ተጻጻፍን። በመጨረሻም ከብዙ ውትወታ በኋላ ከእርሷ ጋር ለመገናኘት ድፍረት አገኘሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ ጊሴላ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ በተባለው መጽሐፍ በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ አስጠናችኝ። ጥናታችንን ስንጨርስ በአካባቢው ባለው የመንግሥት አዳራሽ በሚደረግ ስብሰባ ላይ እንድገኝ ጋበዘችኝ። በዚህ ጊዜ የምለው ጠፋኝ። ከቤት ሳልወጣ አራት ዓመት ሆኖኝ ስለነበር ወደ ውጭ የመውጣቱ ሐሳብ በጣም አስፈራኝ።

“ጊሴላ በጣም በትዕግሥት ነበር የያዘችኝ። ምንም የሚያስፈራ ነገር እንደሌለና አብራኝ ወደ ስብሰባ እንደምትሄድም ነገረችኝ። በመጨረሻ በሐሳቧ ተስማማሁ። ወደ መንግሥት አዳራሹ ስንደርስ ብርክ ብርክ ይለኝና ያልበኝ ጀመር። ማንንም ሰው ሰላም ማለት አልቻልኩም። የሆነ ሆኖ በስብሰባዎች ላይ መገኘት ለመቀጠል የወሰንኩ ሲሆን ጊሴላም ያለማቋረጥ በየሳምንቱ እየመጣች ትወስደኝ ነበር።

“በውስጤ የሚሰማኝን የመረበሽ ስሜት እንዳሸንፍ ለመርዳት ጊሴላ ወደ ስብሰባ ይዛኝ የምትሄደው ቀደም ብላ ነበር። በር ላይ እንቆምና እያንዳንዱ ሰው ሲመጣ ሰላምታ እንሰጣለን። እንዲህ በማድረግ ሁሉንም ሰው በአንድ ጊዜ ከማግኘት ይልቅ ተራ በተራ ከአንድ ወይም ከሁለት ሰው ጋር ብቻ እገናኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ አልችልም ብዬ ሳስቸግራት ጊሴላ ማቴዎስ 19:​26ን ትጠቅስልኝ ነበር:- ‘ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል።’

“ቀላል ባይሆንም እንኳን ውሎ አድሮ ከዚህ የበለጠ ብዙ ሕዝብ በሚገኝበት የወ​ረዳ ስብሰባ ላይ መገኘት ቻልኩ። ለእኔ ምንኛ ትልቅ መሻሻል ነበር! በመስከረም 1995 ሽማግሌዎቹን ከቤት ወደ ቤት በማገልገል መሳተፍ እንደምፈልግ ለማነጋገር ድፍረት አገኘሁ። ከስድስት ወር በኋላ በሚያዝያ 1996 ለይሖዋ ያደረግሁትን ውሳኔ በውኃ ጥምቀት አሳየሁ።

“በቅርቡ አንድ ሰው እንዲህ ለማድረግ የሚያስችል ድፍረት እንዴት እንዳገኘሁ ሲጠይቀኝ ‘በውስጤ ካለው ፍርሃት ይልቅ ይሖዋን ለማስደሰት ያለኝ ፍላጎት ይበልጣል’ ስል መለስኩለት። አሁንም ቢሆን አልፎ አልፎ የመንፈስ ጭንቀት የሚሰማኝ ቢሆንም የዘወትር አቅኚ ሆኜ ማገልገሌ ደስታ ጨምሮልኛል። ያሳለፍኩትን ሳስታውስ ከጊሴላ ሐሳብ ጋር መስማማት ግድ ይሆንብኛል። አሁን ለእኔ የሚያስብልኝና ‘ኃይል የሚሰጠኝ’ ጓደኛ አግኝቻለሁ።”​—⁠ፊልጵስዩስ 4:​13

[በገጽ 8 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

“በውስጤ ካለው ፍርሃት ይልቅ ይሖዋን ለማስደሰት ያለኝ ፍላጎት ይበልጣል”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ