የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 6/15 ገጽ 32
  • ከመኳኳያዎች የሚሻል ነገር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከመኳኳያዎች የሚሻል ነገር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 6/15 ገጽ 32

ከመኳኳያዎች የሚሻል ነገር

ሐዋርያው ጴጥሮስ ሴቶች መልካቸውን ለማስዋብ ስለሚጠቀሙባቸው “ውጫዊ ማጋጌጫዎች” ከተናገረ በኋላ እንዲህ ሲል መክሯል:- “ከዚህ ይልቅ ውበታችሁ በአምላክ ዓይን ከፍተኛ ዋጋ ያለው ገርና ዝግተኛ መንፈስ የተላበሰ፣ ጊዜ የማይሽረው እውነተኛ ውስጣዊ ማንነታችሁን የሚያሳይ ውበት መሆን አለበት።”​—⁠1 ጴጥሮስ 3:​3, 4 ቱዴይስ ኢንግሊሽ ቨርሽን

ሐዋርያው እንዲህ ስላለው ውጫዊ ማጋጌጫ ሲጽፍ ኮስሞስ የሚለውን የግሪክኛ ቃል የተጠቀመ ከመሆኑም በላይ ይህ ቃል “መልክን ማስዋብ” የሚል ትርጉም ያለውና “ኮስሜቲክ” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃልም ከዚያ የመጣ መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው። ጴጥሮስ መኳኳያ መጠቀምንና ይህን የመሳሰሉ ለመዋብ የሚያገለግሉ ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ በክርስቲያን ሴቶች ላይ እገዳ መጣሉ ነበር? በአምላክ ቃል ውስጥ እንዲህ ዓይነት መልእክት የሚያስተላልፍ ነገር ጨርሶ አይገኝም። ከዚህ ይልቅ የአምላክ ቃል በዚህ ጉዳይ ላይ የራሳችንን ውሳኔ እንድናደርግ ስለሚፈቅድ በተወሰነ መጠን የምርጫ ልዩነት እንደሚኖር መጠበቅ አለብን።

ይሁን እንጂ የመኳኳያ አጠቃቀሙ ከልክ በላይ ከሆነ ወይም ብዙዎችን ቅር በሚያሰኝ መጠን ከተደረገ የሚያስተላልፈው መልእክት ምንድን ነው? የአሳቢነት ጉድለት፣ ዓይን አውጣነት፣ ቀልሎ መገኘት፣ እዩኝ እዩኝ ባይነት ወይም ራስ ወዳድነት ሊሆን አይችልም? በእርግጥም አንዲት ሴት ለምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት አሳፋሪ ገጽታ ሊያላብሳት ይችላል።​—⁠ከሕዝቅኤል 23:​36-42 ጋር አወዳድር።

ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ‘እግዚአብሔርን እፈራለሁ የምትል’ ሴት መኳኳያዎች ለመጠቀም ከመረጠች መልኳ ለይቶ የሚያሳውቃትን ጤናማ አስተሳሰብ፣ የረጋ መንፈስ፣ ደግነትና ልከኝነት የሚያሳይ እንዲሆን ጥረት ታደርጋለች። እንዲህ ዓይነቶቹ ባሕርያት ክብርና ተወዳጅነት ይጨምርላታል። እንደ እውነቱ ከሆነ ማጋጌጫ ለመጠቀም መረጠች አልመረጠች የሚያስከብር ባሕርይና ውስጣዊ ውበት ታሳያለች። እንዲህ ማድረጓ ከላይ ያሉት የጴጥሮስ ቃላት እንደሚያሳዩት ከመኳኳያዎች የሚሻል ነገር መኖሩን እንደምትገነዘብ ያሳያል።​—⁠1 ጢሞቴዎስ 2:​9, 10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ