የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 8/1 ገጽ 32
  • ዘረኝነት እና ሃይማኖት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዘረኝነት እና ሃይማኖት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 8/1 ገጽ 32

ዘረኝነት እና ሃይማኖት

“በ1978 ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ስመጣ አሜሪካ የዘረኝነትን ችግር ካስወገደች ቆይታለች፤ ጥቁሮችም እኩል የዜግነት መብት አላቸው የሚል እምነት ነበረኝ” ሲል የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ የሆነው ደራሲው ማርክ ማታባኒ ከታይም መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ገልጿል። “በብዙ መንገዶች ይህ እውነት ሆኖ አግ​ኝቸዋለሁ። ደቡብ አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ መቶ ዓመት ወደኋላ ያለች ይመስል ነበር። ከዚያ ግን የሰዎች ልብ ያን ያህል አለመለወጡን ስገነዘብ በጣም ደነገጥኩ።” ይህን አስደንጋጭ እውነታ እንዲገነዘብ ያደረገው ነገር ምንድን ነው?

“አሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ መድልዎ ከሚታይባቸው ሰዓታት አንዱ እሁድ ጠዋት 5 ሰዓት ነው” ሲል ማታባኒ ተናግሯል። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጭምር ሰዎች ሌላ ዘር ካላቸው ሰዎች ጋር በአምልኮ ለመተባበር ፈቃደኛ እንዳልሆኑ አስተውሏል። “በአዘቦቱ ቀናትማ ስለ ሌላው ዘር ምን ሊሰማቸው ይችላል?” ሲል ጠይቋል። ለውጥ የሚያመጣው ዋናው ነገር ትምህርት መሆኑን በመጥቀስ ማታባኒ እንዲህ ብሏል:- “በተማርክ መጠን የሰው ልጆች አንድ መሆናቸውን ትቀበላለህ።”

የይሖዋ ምሥክሮችም መፍትሔው ትምህርት ነው በሚለው ሐሳብ ይስማማሉ። በተለይ ደግሞ በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ትምህርት። አዎን፣ መጽሐፍ ቅዱስ የዘር ጥላቻ በገነነባቸው አገሮች እንኳ ሳይቀር በዘር ጥላቻ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን እንዲያሸንፉ ይረዳቸዋል። በየሳምንቱ በመንግሥት አዳራሾቻቸው ውስጥ የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የያዛቸውን ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ለመማር የተለያየ ዓይነት ዘርና ዜግነት ያላቸው ሰዎች አንድ ላይ ይሰበሰባሉ። በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም። እርስዎም በስብሰባዎቹ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ