የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 10/15 ገጽ 32
  • “ከእምነት የመነጨ የባሕርይ ጽናት”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ከእምነት የመነጨ የባሕርይ ጽናት”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 10/15 ገጽ 32

“ከእምነት የመነጨ የባሕርይ ጽናት”

በጊ ካኖኒሲ ተዘጋጅቶ በ1998 ገበያ ላይ የዋለው ሌ ቴምወ ደ ዤኦቫ ፋስ አ ኢትሌር (የይሖዋ ምሥክሮች ሂትለርን ተጋፈጡ) የተባለው አዲስ የፈረንሳይኛ መጽሐፍ ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮበታል። የታወቁት ፈረንሳዊው የታሪክ ምሁር ፍራንሷ ቤዳሪዳ በመጽሐፉ መቅድም ላይ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “ይህ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው መጽሐፍ ነው። አንድ ዓይነት ክፍተት የሚደፍን ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በትክክለኛው ጊዜ ላይ የወጣም በመሆኑ ነው። . . . በመስኩ ከተሰማሩ ባለሙያዎች በስተቀር የይሖዋ ምሥክሮች በሦስተኛው ራይክ ያዩትን ፍዳ ሌላ ማን ያውቀዋል? ሆኖም በ12 ዓመታት የግዛት ዘመኑ ሁሉ ፋታ የሌለው ጭካኔና ግፍ ደርሶባቸዋል። በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ያለውንም መከራ ቀምሰዋል። እንዲሁም ለእምነታቸውና ለጽኑ አቋማቸው ሲሉ ከፍተኛ መሥዋዕትነት ከፍለዋል። እነዚህን ክርስቲያኖች ታሪክ የረሳቸው ለምንድን ነው? . . .

“አንድ አናሳና ተበታትኖ የሚገኝ ጉዳት የማያስከትል የሃይማኖት ቡድን እንዲህ ዓይነት ጭካኔና በዘዴ የተቀነባበረ ስደት የደረሰበት ለምን ነበር? ይህ መፍትሔ የሚያሻው የአወዛጋቢው ጉዳይ ዓቢይ ገጽታ ነው። አኃዛዊ መረጃ እንደሚያሳየው በድምሩ ከ60 ሚልዮን በላይ ከሆነው የጀርመን ሕዝብ ውስጥ ወደ 20,000 የሚጠጉት የይሖዋ ምሥክሮች በጣም አናሳ የሆነ የሕዝቡን ክፍል የሚወክሉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሕግ አክባሪዎችና በማንም ላይ ስጋት የማይፈጥሩ ሥራቸውን መሥራትና ልጆቻቸውን በሥርዓት ማሳደግ ብቻ የሚፈልጉ ሰላማውያን ዜጎች ነበሩ። . . .

“ይህ ስደት የደረሰው ፖሊስ ከሰነዘረባቸው አካላዊ ጥቃት አንስቶ እስከ ከፍተኛ ጀግንነትና ሰማዕትነት ድረስ የውጫዊ ጫናዎችን ኃይል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመናቸው ባገኙት ውስጣዊ ኃይል መቋቋም በሚችሉ ጥብቅና ድል አድራጊ የሆነ መንፈሳዊ ጽናት ባላቸው አማኞች ላይ ነው።”

ለክርስቲያናዊ እምነታቸው ሲሉ ሃይማኖታዊ አለመቻቻልን ተጋፍጠው ሰማዕት የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች ታሪክ የሰዎችን ስሜት በጥልቅ የሚነካ ነው። ላ ክሯ የተባለ እውቅ የሆነው የፈረንሳይ ካቶሊክ ጋዜጣ ስለ መጽሐፉ በሰጠው ግምገማ ላይ በግልጽ እንዲህ ሲል አክሏል:- “ጊ ካኖኒሲ ስለ እነርሱ ከሚታወቀው አነስተኛ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ማስረጃ አሰባስቧል። ይህ ማስረጃ የያዘው በጣም ቀላል በሆኑ ቃላት የተገለጸ ከእምነት የመነጨ የባሕርይ ጽናት፣ ልጆች እንኳ ሳይቀር እስከ መጨረሻ ድረስ ለእምነታቸው በጽናት መቆማቸው አንድ ሰው በቃላት ሊገልጽ ከሚችለው በላይ ይሆንበታል። የይሖዋ ምሥክሮችን ክርስቲያናዊ አቋም በተመለከተ በጊዜያችን ላለው አወዛጋቢ ጉዳይ ይህ መታሰቢያ መንደርደሪያ ማቅረብ ይኖርበታል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ