“በመንግሥት አዳራሽ ያደረግሁት ቆይታ”
የኮሌጅ ተማሪ የሆነችው ሎረa በአንድ ሃይማኖታዊ ስብሰባ ላይ እንድትገኝና ከዚያም ስለ ታዘበችው ነገር ሪፖርት እንድትጽፍ ተመደበች። እርሷም በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ ለመገኘት መረጠች። ለምታዘጋጀው ጽሑፍም “በመንግሥት አዳራሽ ያደረክሁት ቆይታ” የሚል ርዕስ ሰጠችው። ሎረ በምሥክሮቹ ስብሰባ ላይ ምን የተለየ ነገር ተመለከተች? ከጠቀሰቻቸው በርካታ ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
ልጆች:- “ሁሉም ልጆች ልክ እንደ አዋቂዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ነበሩ። እስካሁን በሄድኩባቸው አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ልጆች የሚሰበሰቡት ከወላጆቻቸው ተለይተው በሰንበት ትምህርት ቤት ነው።”
የዘር ክፍፍል የለም:- “የአብዛኛው የአብያተ ክርስቲያናት ተሳላሚዎች የአንድ ዘር ወይም ጎሳ አባላት ናቸው። . . . በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ግን ምንም ዓይነት ልዩነት የሌለ ሲሆን ሁሉም የሚቀመጡት ተሰበጣጥረው ነው።”
የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ:- “ብዙ ሰዎች ቀርበው አነጋግረውኛል። . . . እንዲያውም አንዳንዶቹ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀምሬ እንደሆነ ጠይቀውኛል። ሆኖም እንደተጫኑኝ ሆኖ አልተሰማኝም። . . . ውሳኔውን የተዉት ለእኔው ነበር።”
ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም:- “በጣም ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ማንም ሰው ምጽዋት እንዲያደርግ አይጠበቅበትም። . . . እኔ በምካፈልባቸው አብያተ ክርስቲያናት ግን ልጆች ከሚሰበሰቡበት ክፍል እንኳ ሳይቀር ምፅዋት ይሰበሰባል።”
በዓለም ዙሪያ ወደ 90,000 የሚጠጉ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች አሉ። ለምን በአቅራቢያህ የሚገኘውን አትጎበኝም?
[የግርጌ ማስታወሻ]
a ስሟ ተቀይሯል።