የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w00 6/1 ገጽ 32
  • ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
w00 6/1 ገጽ 32

ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን

በዛሬው ጊዜ ታማኝነት እምብዛም የማይታይ ነገር ቢሆንም የእውነተኛው አምላክ የይሖዋ አገልጋዮች ተለይተው እንዲታወቁ የሚያደርግ ባሕርይ ነው። ታማኝ ሰው ፈተናዎች ቢደርሱበትም ከእምነቱ ፍንክች አይልም። ከዚህም በላይ ጊዜው የቱንም ያህል ቢረዝም ከአቋሙ አይወላውልም። ለምሳሌ ጥሩ ንጉሥ የነበረውን የሕዝቅያስን ሁኔታ ተመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ “ከእርሱም በኋላ ከእርሱም በፊት ከነበሩት ከይሁዳ ነገሥታት ሁሉ እርሱን የሚመስል አልነበረም” በማለት ይገልጻል። ሕዝቅያስን ከሌሎቹ ነገሥታት ልዩ ያደረገው ምን ነበር? ሐሰተኛ አምላክ በነበረው በሞሎክ አምላኪዎች ቢከበብም ‘ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቋል።’ አዎን፣ ሕዝቅያስ ‘እግዚአብሔርን ከመከተል አልራቀም፣ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዘውን ትእዛዛቱን ጠብቋል።’​—⁠2 ነገሥት 18:​1-6

ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆኖ በመገኘት ረገድ ሌላው ምሳሌ ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። ሐዋርያው ስላከናወነው ነገር በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው ዘገባ ለአምላክ የሙሉ ነፍስ አገልግሎት በማቅረብ ረገድ ያሳየውን የጸና አቋም በማያሻማ ሁኔታ ያስረዳል። ጳውሎስ በምድራዊ ሕይወቱ መገባደጃ ላይ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ” ማለት ችሎ ነበር።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 4:​7

ሕዝቅያስና ጳውሎስ እንዴት ያሉ ግሩም የታማኝነት ምሳሌዎች ናቸው! እኛም ለታላቁ አምላካችን ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆነን በመገኘት እምነታቸውን እንምሰል።​—⁠ዕብራውያን 13:​7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ