የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w00 6/15 ገጽ 32
  • ግፍን ማስወገድ የሚችለው ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ግፍን ማስወገድ የሚችለው ማን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
w00 6/15 ገጽ 32

ግፍን ማስወገድ የሚችለው ማን ነው?

መስከረም 1999 የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን በ54ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙትን ልዑካን ተቀብለው ነበር። ዘ ቶሮንቶ ስታር ላይ በወጣው ዘገባ መሠረት ለዓለም መሪዎች የሚከተለውን ፈታኝ ሁኔታ ደቅነውባቸው ነበር:- “በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከሚሰጠው የአዘኔታ ቃላት የበለጠ ነገር ማግኘት ይፈልጋሉ። ከሚፈጸምባቸው የግፍ እሽክርክሪት ተላቀው ወደ ብልጽግና የሚያመራ አስተማማኝ ጎዳና እንዲጀምሩ ለማስቻል እውነተኛና ዘላቂ የማረጋገጫ ቃል ያስፈልጋቸዋል።”

ተመድና አባል አገሮቹ ግፍ እንዲወገድ ለማድረግ የሚያስችል “እውነተኛና ዘላቂ የማረጋገጫ ቃል” መስጠት ይችላሉን? ስታር ባቀረበው በዚያው ዘገባ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን እንዲህ ማለታቸው ተጠቅሷል:- “በዚህ መቶ ዘመን የፈሰሰውን ደም መለስ ብለን ካሰብን በኋላ ‘ካሁን በኋላስ ፈጽሞ አይደገምም’ ብሎ መናገሩ ቀላል እንደሆነ እናውቀዋለን፤ ሆኖም ይህን ዕውን ማድረግ እጅግ አዳጋች ነው።” አክለውም “አጉል ተስፋ መስጠት ርኅራኄ የለሽ ከመሆን ተለይቶ አይታይም” ብለዋል።

ከ2, 500 ዓመታት በፊት ነቢዩ ኤርምያስ ሰዎች የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ እንዲህ ብሏል:- “አቤቱ፣ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፣ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም።” (ኤርምያስ 10:​23) ታዲያ ግፍ ፈጽሞ አይወገድም ማለት ነው?

ኢሳይያስ 60:​18 ላይ እንደምናነበው አምላክ እንዲህ የሚል ማረጋገጫ ሰጥቶናል:- “ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፣ በዳርቻሽም ውስጥ ጉስቁልናና ቅጥቃጤ አይሰማም።” አምላክ በግዞት የነበሩትን ሕዝቦቹን ወደ አገራቸው በመለሳቸው ጊዜ ይህ ትንቢት የመጀመሪያ ፍጻሜውን አግኝቷል። ከዚህም በላይ በእኛ ዘመን ታላቅ ፍጻሜውን አግኝቷል። ይሖዋ አምላክ ‘አጉል ተስፋ መስጠቱ’ አይደለም። ሁሉን ቻይና የሰው ልጆች ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን “የግፍን እሽክርክሪት” ለማስቆም ከሁሉ በተሻለ ቦታ ላይ የሚገኘው እርሱ ብቻ ነው። በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ሰላም ይሰፍናል። ግፍ ለዘላለም ይወገዳል!​—⁠ዳንኤል 2:​44

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ