የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 2/1 ገጽ 32
  • “ለእምብርትህ ፈውስ ይሆንልሃል”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለእምብርትህ ፈውስ ይሆንልሃል”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 2/1 ገጽ 32

“ለእምብርትህ ፈውስ ይሆንልሃል”

የሰውን ዘር የሚያጠቁ አብዛኞቹ በሽታዎች እንደ ፍርሃት፣ ሐዘን፣ ቅናት፣ ብስጭት፣ ጥላቻና የጥፋተኝነት ስሜት ከመሳሰሉ ስሜታዊ ውጥረቶች እንደሚመነጩ ይታመናል። ከዚህ አንፃር ‘ይሖዋን መፍራት’ “ለሥጋህ [“ለእምብርትህ፣” NW ] ፈውስ ለአጥንትህም ጠገን” ነው የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር ምንኛ ያጽናናል!​—⁠ምሳሌ 3:​7, 8

አጥንት የሰውነት ምሰሶ ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው በተለይም ጥልቅ በሆኑ ስሜቶች የሚነካውን የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ለማመልከት “አጥንት” የሚለውን ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል። ሆኖም ይሖዋን መፍራት “ለእምብርትህ ፈውስ” የሚሆነው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እዚህ ላይ “እምብርት” ተብሎ ስለተጠቀሰው ቃል ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። አንድ ተንታኝ “እምብርት” “በሰውነት ማእከላዊ” ቦታ ስለሚገኝ በጣም አስፈላጊ የሰውነት አካላትን በሙሉ ሊወክል ይችላል ብለዋል። ሌላው ምሁር ደግሞ “እምብርት” የሚለው ቃል በ⁠ሕዝቅኤል 16:​4 ላይ እንደተሠራበት እትብት ማለት ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል። እንደዚያ ከሆነ ምሳሌ 3:​8 ራሱን መመገብ የማይችል ፅንስ ሙሉ በሙሉ የእናቱ ጥገኛ እንደሆነው ሁሉ እኛም የአምላክ ጥገኞች እንደሆንን የሚያስገነዝብ ሊሆን ይችላል። ሌላው አመለካከት ደግሞ “እምብርት” የሰውነትን ጡንቻዎችና ጅማቶች ሊያመለክት ይችላል የሚል ነው። በዚህ ጥቅስ ላይ እነዚህ የሰውነት አካላት ጠንካራ ከሆነው የአካል ክፍል ይኸውም “ከአጥንት” ጋር ተወዳድረዋል።

ትክክለኛ ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን አንድ ነገር እሙን ነው። ይሖዋን ላለማሳዘን መፍራት የጥበብ መንገድ ነው። ከአምላክ የአቋም ደረጃዎች ጋር ተስማምቶ መኖር አሁንም ቢሆን በአካል ጤነኞች እንድንሆን ሊረዳን ይችላል። ከዚህም በላይ የይሖዋን ሞገስ ያስገኝልናል። ይህ ደግሞ ይሖዋ በቅርቡ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ በአካልም በስሜትም ፍጹም ጤንነት ወደምናገኝበት ፍጻሜ ወደሌለው ሕይወት ይመራናል።​—⁠ኢሳይያስ 33:​24፤ ራእይ 21:​4፤ 22:​2

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

Dr. G. Moscoso/SPL/Photo Researchers

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ