የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 11/15 ገጽ 32
  • “በአምላክ መንግሥት እንገናኛለን”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በአምላክ መንግሥት እንገናኛለን”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 11/15 ገጽ 32

“በአምላክ መንግሥት እንገናኛለን”

“ውድ ጓደኛዬ ሩፐርት! ዛሬ የሞት ቅጣት ተበይኖብኛል። ስለእኔ አትዘን። ለአንተና ለቤተሰቡ ሁሉ ፍቅራዊ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። በአምላክ መንግሥት እንገናኛለን።”

እነዚህ ፍራንትስ ደሮዝግ ሰኔ 8, 1942 በናዚ ወታደሮች ከመገደሉ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የጻፋቸው ቃላት ናቸው። የተገደለው ለምን ነበር?

በስሎቬንያ መሪቦር ናሽናል ሊበሬሽን ሙዚየም ውስጥ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በቀጥቃጭነት ሙያ የሚተዳደረው ይህ የ38 ዓመት ሰው ጀርመን ትቆጣጠራት በነበረችው ስሎቬንያ በሚገኘው ቬርሞንሻፍት የተባለ የጀርመን የውትድርና ማዕከል ለመቀላቀል ፈቃደኛ አልነበረም። ቢበልፎሸር (በወቅቱ በዚያ አካባቢ የነበሩ የይሖዋ ምሥክሮች የሚታወቁበት ስም ነው) ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ነበር። የአምላክ መንግሥት ተገዢ እንደሆነ በመግለጽ በኢሳይያስ 2:​4 ላይ ባሉት ቃላት መሠረት የናዚን የጦርነት እንቅስቃሴ ለመደገፍ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።​—⁠ማቴዎስ 6:33

ፍራንትስ የትውልድ መንደሩ በሆነችው ፐቱይ በአምላክ መንግሥት ምሥራች ቀናተኛ ሰባኪነቱ የታወቀ ነበር። (ማቴዎስ 24:14) ብዙ መከራዎች ቢገጥሙትም በግንቦት 1942 ተይዞ እስከታሰረበት ጊዜ ድረስ ምሥራቹን ያለማሰለስ ሰብኳል።

ብዙ የስሎቬንያ ተወላጅ የሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች በናዚዎች ከፍተኛ ስደት ደርሶባቸዋል። በሃይማኖታዊ እምነታቸው ምክንያት ከተገደሉት መካከል ፍራንትስ የመጀመሪያው ነው። እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ ፍራንትስም “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” በሚሉት ቃላት ተጽናንቶ ነበር። (ሥራ 14:22) ያቺ ሰማያዊ መንግሥት እውን እንደምትሆን የነበረው እምነት “በአምላክ መንግሥት እንገናኛለን” ሲል በተናገራቸው የመጨረሻ ቃላት ተንጸባርቋል።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Franc Drozg: Photo Archive-Museum of National Liberation Maribor, Slovenia; letter: Original kept in Museum of National Liberation Maribor, Slovenia

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ