የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 12/15 ገጽ 32
  • ‘ዓይኖችህን የምትኳለው ኩል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ዓይኖችህን የምትኳለው ኩል’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 12/15 ገጽ 32

‘ዓይኖችህን የምትኳለው ኩል’

ይህ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በትንሿ እስያ ይገኝ ለነበረው የሎዶቅያ የክርስቲያን ጉባኤ ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘው መድኃኒት ነበር።

ኢየሱስ ‘እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ግዛ’ ብሏል። ይህ ሰብዓዊ የዓይን ሕመም ሳይሆን ሕክምና የሚያስፈልገው መንፈሳዊ መታወር ነበር። የሎዶቅያ ክርስቲያኖች በቁሳዊ ሀብት ከበለጸገችው ከተማቸው በሚደርስባቸው ተጽዕኖ ምክንያት ለትክክለኛ መንፈሳዊ ፍላጎታቸው ቸልተኛ ሆነው ነበር።

ለገጠማቸው አጥርቶ የማየት ችግር ምክንያት የሆነው ይህ እንደሆነ ሲናገር ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “ሀብታም ነኝና ባለ ጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፣ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን [አታውቅም]።” የጉባኤው አባላት ባይገነዘቡትም ፈዋሽ “ኵል” ያስፈልጋቸው ነበር። ይህ ኩል የሚገኘው ደግሞ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርትና ተግሣጽ ራስን በማስገዛት ብቻ ነው። ኢየሱስ ‘ከእኔ ግዛ’ ብሏቸዋል።​—⁠ራእይ 3:17, 18 በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።

በሎዶቅያ የነበሩ ክርስቲያኖች በዙሪያቸው ያለው ፍቅረ ነዋይ የተጠናወተውና ተድላን የሚያሳድድ ዓለም ያለልክ ምናልባትም ሳይታወቃቸው ተጽዕኖ እንዳያሳድርባቸው መጠንቀቅ እንደነበረባቸው ሁሉ ዛሬ ያሉ እውነተኛ ክርስቲያኖችም ተመሳሳይ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ‘እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከኢየሱስ ግዛ’ የሚለው ምክር ጤናማ መንፈሳዊ አመለካከትን ጠብቆ ለማቆየት የሚያስፈልገው ምን እንደሆነ ይጠቁማል።

ይህ “ኩል” የሚገዛ መሆኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ወጪ ይጠይቃል። የአምላክን ቃል ለማጥናትና በሱም ላይ ለማሰላሰል ጊዜ ያስፈልጋል። መዝሙራዊው እንዳረጋገጠልን ይህ ቃል “ብሩህ ነው፣ [መንፈሳዊውን] ዓይንም ያበራል።”​—⁠መዝሙር 19:​8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ