የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w02 10/15 ገጽ 32
  • “ለወደፊቱ ሕይወትህ በጥበብ ወስን”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለወደፊቱ ሕይወትህ በጥበብ ወስን”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
w02 10/15 ገጽ 32

“ለወደፊቱ ሕይወትህ በጥበብ ወስን”

“አብዛኛው የሰው ዘር የወጣትነት እድሜውን የሚጠቀምበት የኋለኞቹን ዓመታት መራራ በሚያደርግበት መንገድ ነው።” ይህንን የተናገሩት ዣ ዲ ላ ብሮሪ የተባሉ አንድ የ17ኛው መቶ ዘመን ፈረንሳዊ ደራሲ ናቸው። በእርግጥም በሐሳቡ የሚወላውል አንድ ወጣት በተከፈቱለት አጋጣሚዎች ለመጠቀም ያመነታ ይሆናል። ይህም ኃዘንና ብስጭት ያስከትልበታል። በሌላው በኩል ደግሞ ሐሳበ ግትር የሆነ ወጣት የኋላ ኋላ ደስታ የሚያሳጣውን የሕይወት ጎዳና በመምረጥ ጥበብ የጎደለው እርምጃ ይወስድ ይሆናል። ያም ሆነ ይህ ትክክልና ተገቢ የሆነውን ሳያደርጉ መቅረትም ሆነ ወንጀል ወይም መጥፎ ድርጊት መፈጸም ይህ ነው የማይባል መከራ ሊያስከትል ይችላል።

እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ እንዳይደርስ መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው? በወጣትነት ሊያጋጥም የሚችለውን በሐሳብ የመወላወል ችግር አስመልክቶ የአምላክ ቃል ሲያስጠነቅቅ “የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ” በማለት ይናገራል። (መክብብ 12:​1) ወጣት ከሆንክ ስለ “ፈጣሪህ” ለመማር አሁኑኑ አዎንታዊ እርምጃ ውሰድ።

መጽሐፍ ቅዱስ ወጣቶች የግዴለሽነትን ባሕርይ እንዲያስወግዱ የሚረዳቸው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ “ምክርን ስማ፣ ተግሣጽንም ተቀበል በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ” በማለት ይናገራል። (ምሳሌ 19:​20) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ በወጣትነት ጊዜም ሆነ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ግዴለሽ ወይም ዓመፀኛ በመሆን አምላካዊውን ጥበብ ችላ ማለት አስከፊ መዘዝ እደሚያስከትል በግልጽ ይናገራል። (ምሳሌ 13:​18) ከዚህ በተቃራኒው መለኮታዊ መመሪያዎችን መከተል ግን ‘ብዙ ዘመናት፣ ረጅም ዕድሜና ሰላም’ ማለትም አስደሳችና አርኪ ሕይወት ያስገኛል።​—⁠ምሳሌ 3:​2

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ