የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w03 2/15 ገጽ 32
  • “ስለ አምላክ ብዙም አላውቅም ነበር”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ስለ አምላክ ብዙም አላውቅም ነበር”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
w03 2/15 ገጽ 32

“ስለ አምላክ ብዙም አላውቅም ነበር”

በሕንድ ከራላ በተባለች ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር:- “ባለፈው ዓመት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቴ ድረስ እየመጡ ስለ አምላክ መንግሥት የሚናገረውን ምሥራች ያካፍሉኝ ነበር። ለስምንት ዓመታት ካቶሊክ የነበርኩ ብሆንም ስለ አምላክ ብዙም አላውቅም ነበር። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ግን ብዙ ነገር ተምሬያለሁ።” ሲቀጥልም እንዲህ አለ:- “መጠበቂያ ግንብ በ139 [በአሁኑ ወቅት 146] ቋንቋዎች የሚታተም መሆኑ በጣም አስደስቶኛል። ብዙ ሰዎች ስለ አምላክ የሚናገረውን ምሥራች በቋንቋቸው እንዲሰሙ መደረጉ በጣም የሚያስደስት ነው።”

በርካታ ፈላስፋዎች አምላክን ማወቅ እንደማይቻል ቢናገሩም እንኳ ሐዋርያው ጳውሎስ አምላክን ማወቅ እንደሚቻል በግልጽ አሳይቷል። ጳውሎስ “ለማይታወቅ አምላክ” መሠዊያ ሠርተው ያመልኩ የነበሩትን አንዳንድ ሰዎች ጨምሮ በአቴና ለነበሩት ሰዎች ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር:- “ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ። ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ . . . ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና . . . በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ።”​—⁠ሥራ 17:23-26

ጳውሎስ ፈጣሪ ‘ከእያንዳንዳችን የራቀ ስላይደለ’ እርሱን ለማወቅ ጥረት እንዲያደርጉ አድማጮቹን አሳስቧቸዋል። (ሥራ 17:27) እርስዎም እውነተኛውን አምላክና ማራኪ የሆኑትን ባሕርያቱን ማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች ሊረዱዎት ፈቃደኞች ናቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ