የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w03 5/15 ገጽ 32
  • የዘላለም ሕይወትን ምረጥ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዘላለም ሕይወትን ምረጥ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
w03 5/15 ገጽ 32

የዘላለም ሕይወትን ምረጥ

ሰዎች የአሁኑን ጊዜ ያህል የተለያዩ ምርጫዎችን የማድረግ አጋጣሚ ያገኙበት ዘመን የለም። ለምሳሌ ያህል የምንለብሰውን ልብስ፣ የምንመገበውን ምግብ፣ የምንሠማራበትን የሥራ መስክና የምንኖርበትን ቦታ እንመርጣለን። በአብዛኛው የዓለም ክፍል የትዳር ጓደኛን መምረጥም የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ለመላው የሰው ዘር ከምንም ነገር የላቀ አንድ ምርጫ ያቀርባል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “መልካም ሥራ ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ ያደረገ ሰው፣ በሕይወት ይኖራል፤ ስሕተት በማድረግ የሚጸና ግን ይሞታል።” (ምሳሌ 11:​19 የ1980 ትርጉም ) እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” በማለት ተናግሯል።​—⁠ዮሐንስ 17:3

አዎን፣ ፈጣሪያችን ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራውን ጎዳና ለመከተል እንድንመርጥ ግብዣ አቅርቦልናል! የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

መጽሐፍ ቅዱስ “በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ” በማለት ይናገራል። (ምሳሌ 12:28) እኛም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን ጎዳና ከሚከተሉት ጻድቃን መካከል ልንሆን እንችላለን። እንዴት? ሕይወታችንን ከአምላክ ፈቃድና ትእዛዛት ጋር በማስማማት ነው። (ማቴዎስ 7:​13, 14) እንግዲያው ትክክለኛ ምርጫ በማድረግ አምላክ ያዘጋጀልንን የዘላለም ሕይወት ስጦታ እንቀበል።​—⁠ሮሜ 6:​23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ