የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w03 10/1 ገጽ 32
  • “የመውጊያውን ብረት” ትቃወማለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የመውጊያውን ብረት” ትቃወማለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
w03 10/1 ገጽ 32

“የመውጊያውን ብረት” ትቃወማለህ?

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የበሬ መውጊያ የጭነት ከብቶችን ለመንዳትና ለመምራት የሚያገለግል ጫፉ ላይ ሹል ብረት ያለው ረጅም ዘንግ ነበር። ከብቱ የመውጊያውን ብረት በመቃወም በእልህ መልሶ ቢገፋው ምን ይደርስበታል? በራሱ ላይ ሥቃይ ይጨምራል እንጂ እረፍት አያገኝም።

ከሞት የተነሣው ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን ደቀ መዛሙርት ለማሳሰር በጉዞ ላይ ለነበረው ሳውል ለተባለ ሰው በተገለጠ ጊዜ ስለ መውጊያው ብረት ተናግሯል። ሳውል በሚያጥበረብር ብርሃን መሀል “ሳውል ሳውል፣ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” ብሎ ኢየሱስ ሲናገር ሰማ። ሳውል ክርስቲያኖችን ሲያንገላታ ከአምላክ ጋር እየተዋጋ ያለ ያህል ነበር፤ ይህ ደግሞ ይጎዳዋል እንጂ አይጠቅመውም።​—⁠ሥራ 26:14

እኛም ሳናውቀው “የመውጊያውን ብረት” እየተቃወምን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የጠቢባን ቃል” በትክክለኛው አቅጣጫ እንድንጓዝ ከሚመራን የበሬ መውጊያ ጋር ተመሳስሏል። (መክብብ 12:11) በአምላክ ቃል ውስጥ ያለው በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ምክር እኛ ከፈቀድንለት በትክክለኛው አቅጣጫ እንድንጓዝ ሊያነሳሳንና ሊመራን ይችላል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) መጽሐፉ የሚሰጠንን መመሪያ መቃወማችን ጉዳት ያስከትልብናል።

ሳውል ኢየሱስ የነገረውን ተቀብሎ አካሄዱን በመለወጥ ሐዋርያው ጳውሎስ በመባል የሚታወቅ ተወዳጅ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል። እኛም የሚሰጠንን መለኮታዊ ምክር መከተላችን ዘላለማዊ በረከት ያስገኝልናል።​—⁠ምሳሌ 3:1-6

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል ምንጭ]

L. Chapons/Illustrirte Familien-Bibel nach der deutschen Uebersetzung Dr. Martin Luthers

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ