የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w05 2/1 ገጽ 32
  • “ተግታችሁ ጠብቁ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ተግታችሁ ጠብቁ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
w05 2/1 ገጽ 32

“ተግታችሁ ጠብቁ”

በጥንት ጊዜያት በከተማ ወይም በመቅደስ፣ አንዳንዴም በግል መኖሪያ ቤት በሮች ላይ ዘብ ጠባቂዎች ይቆሙ ነበር። እነዚህ ዘበኞች ምሽት ላይ በሮቹን ከመዝጋት በተጨማሪ በጠባቂነት የማገልገል ኃላፊነት ነበራቸው። የከተማው ደኅንነት የተመካው ጠባቂዎቹ አደጋ ሲመጣ ተመልክተው ለሕዝቡ በሚሰጡት ማስጠንቀቂያ ላይ በመሆኑ ከባድ ኃላፊነት ነበረባቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በረኞች ተብለው የሚጠሩት ዘበኞች የሚያከናውኑትን ሥራ ያውቅ ነበር። በአንድ አጋጣሚ ደቀ መዛሙርቱን በበረኞች የመሰላቸው ሲሆን እየቀረበ የነበረውን የአይሁድ ሥርዓት መጥፋት በንቃት እንዲጠባበቁ አበረታቷቸው ነበር። እንዲህ አላቸው:- ‘ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ይህም ቤቱን ለአገልጋዮቹ ትቶ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል። እንግዲህ የቤቱ ባለቤት መቼ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ።’—ማርቆስ 13:33-35

ከዚህ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ መጠበቂያ ግንብ የተባለው ይህ መጽሔት ኢየሱስ “ተግታችሁ ጠብቁ” በማለት የሰጠውን ማበረታቻ ከ125 ለሚበልጡ ዓመታት ለሌሎች ሲያስተላልፍ ቆይቷል። እንዴት? በዚሁ መጽሔት ገጽ 2 ላይ እንደተገለጸው “የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ የሆኑትን የዓለም ሁኔታዎች ትኩረት ሰጥቶ ይከታተላል። የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ጨቋኞችን በማጥፋት ምድርን ወደ ገነትነት የሚለውጥ መሆኑን በማስታወቅ ሰዎችን ሁሉ ያጽናናል።” በመላው ዓለም በ150 ቋንቋዎች ከ25,600,000 በሚበልጡ ቅጂዎች የሚታተመውን መጠበቂያ ግንብን ያህል በስፋት የሚሰራጭ ሃይማኖታዊ መጽሔት የለም ለማለት ይቻላል። የጥንት በር ጠባቂዎች ያደርጉት እንደነበረው የይሖዋ ምሥክሮችም ‘የቤቱ ባለቤት’ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በዚህ ሥርዓት ላይ የሚፈርድበት ጊዜ መቅረቡን በዚህ መጽሔት አማካኝነት በሁሉም ሥፍራ ለሚገኙ ሰዎች በመንገር በመንፈሳዊ ‘ተግተው እንዲጠብቁ’ እያሳሰቡ ነው።—ማርቆስ 13:26, 37

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ