የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w05 7/15 ገጽ 32
  • “እምነታቸውን አልካዱም”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “እምነታቸውን አልካዱም”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
w05 7/15 ገጽ 32

“እምነታቸውን አልካዱም”

ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ “ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ፤ ብፁዓን ናችሁ” በማለት ነግሯቸዋል። (ማቴዎስ 5:11) በዛሬው ጊዜ የሚገኙት የይሖዋ ምሥክሮች የክርስቶስን ትምህርትና ምሳሌ በመከተል “ከዓለም ባለመሆናቸው” እንዲሁም በምንም ዓይነት ሁኔታ ሥር ቢሆኑም ለአምላክ ያላቸውን የታማኝነት አቋም በመጠበቃቸውና ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ገለልተኛ በመሆናቸው ደስተኞች ናቸው።—ዮሐንስ 17:14፤ ማቴዎስ 4:8-10

በኢስቶኒያ የሚገኙትን ጨምሮ በቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት የነበሩ የይሖዋ ምሥክሮች የወሰዱትን የጸና አቋም በተመለከተ የሉተራን የሃይማኖት ምሁር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሆኑት ቶማስ ፖል ኪሪክ ከሴት ኩላ (በመንደሩ መሃል ያለችው ቤተ ክርስቲያን) በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ በማለት ጽፈዋል:- “ሚያዝያ 1, 1951 ማለዳ ላይ ስለተፈጸመው ሁኔታ የሰሙት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው። የይሖዋ ምሥክሮችንም ሆነ የሚደግፏቸውን ሰዎች በሙሉ ከአገር ለማባረር በታቀደው ዘመቻ መሠረት በጠቅላላ 279 የሚሆኑ ሰዎች ተይዘው ወደ ሳይቤሪያ ተጋዙ . . . ከአገር ላለመባረር ወይም ላለመታሰር ከፈለጉ እምነታቸውን እንደካዱ በሚገልጽ ቅጽ ላይ የመፈረም አጋጣሚ ተሰጥቷቸው ነበር። . . . ቀደም ብለው የታሰሩትን ጨምሮ በጠቅላላ 353 የሚያክሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፤ ከእነዚህም መካከል ቢያንስ 171 የሚሆኑት በጉባኤዎቻቸው ላይ ከመገኘት ያለፈ ተሳትፎ አልነበራቸውም። [የይሖዋ ምሥክሮች] ወደ ሳይቤሪያ ቢጋዙም እንኳ እምነታቸውን አልካዱም። . . . [ከኢስቶኒያ ሉተራን] ቤተ ክርስቲያን አባላት መካከል የይሖዋ ምሥክሮች ዓይነት እምነት ያሳዩት እምብዛም አይደሉም።”

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች በታማኝነት ጸንተው እንዲቆሙና ስደት ቢደርስባቸውም እንኳ ታዛዦች መሆን እንዲችሉ አምላክ እንደሚረዳቸው ሙሉ እምነት አላቸው። ታማኝ በመሆናቸው የሚያገኙት ወሮታ ከፍተኛ መሆኑን ማወቃቸው ያስደስታቸዋል።—ማቴዎስ 5:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ