የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 12/1 ገጽ 32
  • ዳኞች ሊገሠጹ ይችላሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዳኞች ሊገሠጹ ይችላሉ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 12/1 ገጽ 32

ዳኞች ሊገሠጹ ይችላሉ?

በክሮኤሺያ የምትኖር ስላዲያና የተባለች አንዲት የይሖዋ ምሥክር አንዳንድ ተንዘብ ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ ፍርድ ቤት እንድትቀርብ ተጠርታ ነበር። ስላዲያና ሰዓቷን አክብራ በችሎት ፊት ቀረበች። ሆኖም ጉዳዩ የሚመለከተው ሌላኛው ወገን ዘገየ። ስላዲያና ሰው ሁሉ እየጠበቀ ሳለ ምሥክርነት ለመስጠት ፈለገች። ስለዚህ ራሷን እንደምንም አደፋፍራ ዳኛውን አነጋገረቻቸው።

“ጌታዬ፣ በቅርቡ በምድር ላይ ዳኞችም ሆኑ ፍርድ ቤቶች የማይኖሩበት ጊዜ እንደሚመጣ ያውቃሉ?” ስትል ጠየቀቻቸው። እርግጥ ነው፣ ይህን ስትል በአሁኑ ጊዜ ስላሉት ዳኞች መናገሯ ነበር።

ዳኛው አንድም ቃል ሳይሰነዝሩ በግርምት ተመለከቷት። በዚህ ጊዜ ችሎቱ ተጀመረ። ችሎቱ ካለቀ በኋላ ስላዲያና በአንድ ሰነድ ላይ ለመፈረም ቆማ ሳለ ዳኛው ወደ እርሷ ጎንበስ ብለው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ጠየቋት:- “በቅርቡ በምድር ላይ ዳኞችም ሆኑ ፍርድ ቤቶች የማይኖሩበት ጊዜ እንደሚመጣ ስለነገርሽኝ ነገር እርግጠኛ ነሽ?”

ስላዲያናም “አዎን ጌታዬ፤ በጣም እርግጠኛ ነኝ!” ስትል መለሰችላቸው።

ዳኛውም “ምን ማስረጃ አለሽ?” ብለው ጠየቋት።

“ማስረጃው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል” አለች።

ዳኛውም መጽሐፍ ቅዱስ ስለሌላቸው እንጂ ማስረጃውን ቢመለከቱ ደስ እንደሚላቸው ነገሯት። ስለዚህ ስላዲያና መጽሐፍ ቅዱስ ልታመጣላቸው እንደምትችል ነገረቻቸው። የይሖዋ ምሥክሮች ዳኛው ጋር ሄደው መጽሐፍ ቅዱስ ከሰጧቸው በኋላ በየሳምንቱ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ አበረታቷቸው። ዳኛውም የቀረበላቸውን ግብዣ የተቀበሉ ሲሆን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የይሖዋ ምሥክር ሆኑ።

መዝሙር 2:10 [NW] የሚከተሉትን ትንቢታዊ ቃላት ይናገራል:- “አሁንም እናንት ነገሥታት፣ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ዳኞችም፣ ተገሠጹ።” እንደነዚህ ያሉት ሰዎች የይሖዋን ፍቅራዊ መመሪያ በትሕትና መቀበላቸው እንዴት ያስደስታል!

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ስላዲያና እና ዳኛው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ