የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 6/1 ገጽ 26
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • አስደናቂዎቹ የጆሴፈስ የታሪክ ጽሑፎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • “መሲሕን አግኝተናል”!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • መጽሐፍ ቅዱስ​—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ፣ ክፍል 3
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 6/1 ገጽ 26

ይህን ያውቁ ኖሯል?

አይሁዳውያን ለትውልድ ሐረግ መዝገብ ትልቅ ቦታ ይሰጡ የነበረው ለምንድን ነው?

▪ የትውልድ ሐረግ መዝገብ አንድ ሰው ከየትኛው ነገድና ቤተሰብ እንደሆነ ለማወቅ ይጠቅም ነበር። ከዚህም ሌላ ከርስት ክፍፍልና ከውርስ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ረገድ ውሳኔ ለማድረግ ያስፈልግ ነበር። ከሁሉ የበለጠ ደግሞ ተስፋ የተሰጠበትን መሲሕ የዘር ሐረግ ለማወቅ አስችሏል። መሲሑ መምጣት ያለበት ከይሁዳ ነገድ በዳዊት የዘር ሐረግ በኩል እንደሆነ በአይሁዳውያን ዘንድ የታወቀ ነገር ነበር።​—ዮሐንስ 7:42

ዮአኪም ዬሬሚያስ የተባሉት ምሁር “ካህናትና ሌዋውያን የአገልግሎት መብታቸውን የሚያገኙት በውርስ በመሆኑ . . . የዘር ሐረጋቸው ከሌሎች ጋር ሳይቀላቀል መቀጠሉ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ነበር” ብለዋል። የካህናቱ ዘር “ሳይበረዝ ንጹሕ” ሆኖ እንዲቀጥል፣ የካህናት ቤተሰቦችን የሚያገቡ እስራኤላውያን ሴቶች የዘር ሐረጋቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ነበረባቸው። በነህምያ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ሌዋውያን ቤተሰቦች “የየቤተ ሰብ ትውልድ ሐረጋቸውን ከመዝገብ ለማግኘት ፈልገው . . . ሊያገኙት [ስላልቻሉ]” ከክህነት ተከልክለዋል።​—ነህምያ 7:61-65

በተጨማሪም የሙሴ ሕግ “ዲቃላ” ወይም “አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ . . . ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ” የሚል ግልጽ መመሪያ ይዞ ነበር። (ዘዳግም 23:2, 3) በዚህም ምክንያት ዬሬሚያስ አክለው እንደገለጹት “አንድ ሰው ማንኛውንም የዜግነት መብት ማግኘት እንዲችል ያልተበረዘ የዘር ሐረግ እንዳለው ማስረጃ ማቅረብ ነበረበት፤ . . . አንድ ተራ እስራኤላዊ እንኳ አያት ቅድመ አያቶቹን እንዲሁም ከአሥራ ሁለቱ ነገዶች መካከል ከየትኛው እንደሚመደብ ያውቅ ነበር።”

አይሁዳውያን የትውልድ ሐረግ መዝገቦችን የሚያዘጋጁትና ተጠብቀው እንዲቆዩ የሚያደርጉት እንዴት ነበር?

▪ የወንጌል ጸሐፊዎች የሆኑት ማቴዎስና ሉቃስ የኢየሱስን የትውልድ ሐረግ በዝርዝር አስፍረዋል። (ማቴዎስ 1:1-16፤ ሉቃስ 3:23-38) ሌሎች የትውልድ ሐረግ መዝገቦችም እንዲሁ ተጠብቀው ቆይተዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ትንታኔ የሚሰጥ አንድ የአይሁዳውያን ጽሑፍ በኢየሱስ ዘመን ስለኖረ ሂሌል የሚባል ረቢ እንዲህ ይላል፦ “በኢየሩሳሌም በተገኘው የትውልድ ሐረግ ዝርዝሮችን የያዘ ጥቅልል ላይ ሂሌል ከዳዊት የዘር ሐረግ እንደመጣ ተመዝግቧል።” በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው አይሁዳዊ የታሪክ ምሁር ዘ ላይፍ በተሰኘው ሥራው ላይ ቅድመ አያቶቹ ካህናት እንደነበሩና በእናቱ በኩል “የነገሥታት ደም” እንዳለው አስፍሯል። ይህንን መረጃም “በሕዝብ መዛግብት ውስጥ ሰፍሮ” እንዳገኘው ገልጿል።

ጆሴፈስ አጌነስት አፒዮን በተባለው ሥራው ላይ እንደዘገበው የካህናት ቤተሰቦችን የትውልድ ሐረግ መዝገብ እንዲጠብቁ በአደራ ይሰጥ የነበረው “ለአምላክ አገልግሎት ላደሩ የላቀ ሥነ ምግባር ያላቸው ሰዎች” ነው። ዘ ጂዊሽ ኢንሳይክሎፒዲያ እንዲህ ይላል፦ “እነዚህን መዝገቦች የሚጠብቅ ሰው ይመደብ የነበረ ይመስላል፤ እንዲሁም ከትውልድ ሐረግ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን የሚመልስ ችሎት በኢየሩሳሌም ይሰየም [ነበር]።” ከካህናት ወገን ያልሆኑ አይሁዳውያን በአባታቸው የትውልድ ከተማ ይመዘገቡ ነበር። (ሉቃስ 2:1-5) የወንጌል ጸሐፊዎች መረጃቸውን የወሰዱት ከእነዚህ የሕዝብ መዛግብት እንደሆነ ግልጽ ነው። አንዳንድ ቤተሰቦች ደግሞ የራሳቸውን መዝገብ ያስቀምጡ የነበረ ይመስላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ