የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 12/1 ገጽ 6
  • ችግረኞችን መርዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ችግረኞችን መርዳት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ገና አስደሳችና ሰላማዊ እንዲሆን የሚደረግ ጥረት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ለድሆች አሳቢነት እናሳይ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • በቅርቡ ድህነት ፈጽሞ ይወገዳል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የይሖዋ ምሥክሮች ገናን የማያከብሩት ለምንድን ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 12/1 ገጽ 6

ችግረኞችን መርዳት

“ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ ምግቡን ከድኾች ጋር ይካፈላልና።”—ምሳሌ 22:9

አንዳንዶች ገናን የሚያከብሩበት ምክንያት

ኢየሱስ ድሆችን እንዲሁም የታመሙና ችግር ላይ ያሉ ሰዎችን ይረዳ ስለነበረ አንዳንዶች ምሳሌውን መከተል ይፈልጋሉ። ይህን ለማድረግ ከሁሉ የተሻለው ጊዜ ደግሞ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ብዙውን ጊዜ የእርዳታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጥረት በሚያደርጉበት በገና ወቅት እንደሆነ ይሰማቸዋል።

ይህን ማድረግ ተፈታታኝ የሆነው ለምንድን ነው?

በበዓላት ወቅት ብዙ ሰዎች ገበያ ስለሚወጡ፣ ስለሚዝናኑና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ስለሚጠይቁ ጊዜያቸው የተጣበበ ነው። ጊዜያቸው፣ ጉልበታቸው ወይም ገንዘባቸው በእነዚህ ነገሮች ስለሚሟጠጥ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ለእርዳታ ድርጅት የተወሰነ ገንዘብ መስጠት ብቻ ሊሆን ይችላል።

ሊረዱን የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች

“ማድረግ እየቻልህ ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ አትቈጠብ።” (ምሳሌ 3:27) ድሆች እንዲሁም የተራቡና ችግር ላይ የወደቁ ሰዎች እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በገና ሰሞን ብቻ አይደለም። አንድ ሰው እርዳታ እንደሚያስፈልገው ካስተዋልክና ልትረዳው ‘የምትችል ከሆነ’ በዓል እስኪመጣ ለምን ትጠብቃለህ? ደግነትና ርኅራኄ ማሳየትህ መልሶ ይክስሃል።

“ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እንደ ገቢው ሁኔታ የተወሰነ መጠን በቤቱ ያስቀምጥ።” (1 ቆሮንቶስ 16:2) ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ምክር የሰጠው ድሆችን መርዳት ፈልገው ለነበሩ የጥንት ክርስቲያኖች ነው። አንተም ለተቸገሩ ግለሰቦች ወይም የሰበሰበውን ገንዘብ በአግባቡ ለሚጠቀም አንድ የእርዳታ ድርጅት አዘውትረህ መስጠት እንድትችል የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ በየጊዜው ‘ማስቀመጥ’ ትችል ይሆን? በዚህ መንገድ አቅምህ የሚፈቅድልህን ያህል እያደረግህ ለችግረኞች እንደምታስብ ታሳያለህ።

“መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤ ምክንያቱም አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታል።” (ዕብራውያን 13:16) ‘ያለንን ነገር ለሌሎች ከማካፈል’ በተጨማሪ “መልካም ማድረግን” ወይም ሌሎችን የሚጠቅም ተግባር መፈጸምን መርሳት እንደሌለብን ልብ በል። ለምሳሌ ያህል፣ አስተዋይ የሆኑ ወላጆች፣ ልጆቻቸው አረጋውያንን በዕለት ተዕለት ሥራዎች እንዲያግዙ እንዲሁም ካርድ በመላክ፣ ሄዶ በመጠየቅ ወይም ስልክ በመደወል የታመሙ ሰዎችን እንዲያበረታቱና ድሃ ወይም የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ ልጆች አሳቢነት እንዲያሳዩ ያሠለጥኗቸዋል። ልጆች እንዲህ ዓይነት ሥልጠና ከተሰጣቸው በበዓል ወቅት ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ደጎች እና ለጋሶች መሆንን ይማራሉ።

አስተዋይ የሆኑ ወላጆች፣ ልጆቻቸው አረጋውያንን፣ የታመሙ ሰዎችን እንዲሁም ችግረኛ ወይም የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ልጆችን እንዲረዱ ያሠለጥኗቸዋል። በዚህ መንገድ ልጆች በበዓል ወቅት ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ደጎች እና ለጋሶች መሆንን ይማራሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ