የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | አምላክ ምን አድርጎልሃል?
ሊያመልጥህ የማይገባ ልዩ በዓል
ኢየሱስ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት በነበረው ምሽት ታማኝ ተከታዮቹን እሱ ያቀረበውን መሥዋዕት መታሰቢያ አድርገው እንዲያከብሩ አዝዟቸዋል። ያልቦካ ቂጣውንና ቀዩን የወይን ጠጅ ለሐዋርያቱ በማቅረብ የጌታ ራት እየተባለ የሚጠራውን በዓል ካቋቋመ በኋላ “ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” በማለት አዘዛቸው።—ሉቃስ 22:19
በመላው ዓለም ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ ለማክበር ይሰበሰባሉ። በ2014 መታሰቢያ በዓሉ የሚውለው ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. (ሚያዝያ 14, 2014) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው።
በዚህ ዕለት በምናደርገው ስብሰባ ላይ እንድትገኝ በአክብሮት ተጋብዘሃል፤ በስብሰባው ላይ የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞት ስላለው ትልቅ ትርጉም ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል። በዚህ በዓል ላይ ለመገኘት ምንም ዓይነት ክፍያ አይጠየቅም። ሙዳየ ምፅዋትም አይዞርም። ይህን መጽሔት የሰጠህ ሰው የመታሰቢያው በዓል በአካባቢህ የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ ሊነግርህ ይችላል፤ አለዚያም jw.org/am የተባለውን ድረ ገጽ ተመልከት። እባክህ ቀኑን በማስታወሻህ ላይ አስፍር፤ በዚህ ዕለት እንደምትገኝ ተስፋ እናደርጋለን።