የርዕስ ማውጫ
ከሰኔ 27, 2016–ሐምሌ 3, 2016 ባለው ሳምንት
በወረስነው ኃጢአት ምክንያት፣ አንዳንድ ጊዜ በወንድሞቻችን ላይ ቅሬታ እንዲያድርብን የሚያደርጉ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል። ይህ ርዕስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ አለመግባባቶችን መፍታት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
ከሐምሌ 4-10, 2016 ባለው ሳምንት
8 “ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”
ኢየሱስ በማቴዎስ 24:14 ላይ የተናገረውን ትንቢት በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ እየፈጸሙ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች ብቻ እንደሆኑ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በዚህ ርዕስ ላይ እንመለከታለን። በተጨማሪም “ሰው አጥማጆች” መሆን ምን እንደሚያካትት ይብራራል።—ማቴ. 4:19
ከሐምሌ 11-17, 2016 ባለው ሳምንት
ውሳኔ የምታደርጉበት ጊዜ እንዲሁ መልካም መስሎ የታያችሁን ታደርጋላችሁ? አሊያም ደግሞ ሌሎች እንዲወስኑላችሁ ታደርጋላችሁ? በይሖዋ አምላክ አስተሳሰብ መመራት የተሻለ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።
ከሐምሌ 18-24, 2016 ባለው ሳምንት
18 መጽሐፍ ቅዱስ አሁንም ሕይወትህን እየለወጠው ነው?
ከመጠመቅህ በፊት ትላልቅ ለውጦች አድርገህ ይሆናል፤ ይሁንና አሁን ክርስቲያናዊ ባሕርያትህን እያሻሻልክ መሄድ ከዚያ ይበልጥ ከባድ ሆኖብሃል? እንዲህ ያለ ተፈታታኝ ሁኔታ የሚያጋጥመን ለምን እንደሆነ እንዲሁም በአምላክ ቃል በመታገዝ ይሖዋን የሚያስደስቱ ባሕርያት ማዳበራችንን መቀጠል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይህ ርዕስ ያብራራል።
ከሐምሌ 25-31, 2016 ባለው ሳምንት
ይህ ርዕስ ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ ዝግጅቶች እንዲያመልጡን ሊያደርግ የሚችልን አደገኛ አስተሳሰብ ይጠቁመናል። በዚህ አደገኛ ወጥመድ ላለመውደቅ ምን ማድረግ እንደምንችል ብሎም ከሚቀርብልን መንፈሳዊ ምግብ ሁሉ ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።
28 ከታሪክ ማኅደራችን