የርዕስ ማውጫ
ከነሐሴ 29, 2016–መስከረም 4, 2016 ባለው ሳምንት
7 ቁሳዊ ነገሮችን ሳይሆን የአምላክን መንግሥት ፈልጉ
ኢየሱስ ቁሳዊ ነገሮችን ከመፈለግ ይልቅ ‘ከሁሉ አስቀድመን የአምላክን መንግሥት’ እንድንፈልግ አስተምሮናል። ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረት መስጠት እንድንችል ከፍቅረ ንዋይ ወጥመድ ራሳችንን መጠበቅና ኑሯችንን ቀላል ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ወቅት ከተናገረው ሐሳብ ውስጥ በማቴዎስ 6:25-34 ላይ የሚገኘውን የሚያበረታታ ነጥብ እስቲ እንመልከት።
ከመስከረም 5-11, 2016 ባለው ሳምንት
13 ‘ምንጊዜም ነቅተን መጠበቅ’ ያለብን ለምንድን ነው?
በመጨረሻው ዘመን የምንኖር ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ “ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ” በማለት የሰጠውን ምክር በቁም ነገር ልንመለከተው ይገባል። (ማቴ. 24:42) ይህን ለማድረግ ደግሞ ኢየሱስ የሚመጣበትን ጊዜ ነቅተን ከመጠበቅ ሊያዘናጉን የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ ይኖርብናል። ይህ የጥናት ርዕስ ሊያዘናጉን የሚችሉ ነገሮችን እንዴት ማስወገድ እንደምንችል ያብራራል።
ከመስከረም 12-18, 2016 ባለው ሳምንት
ከመስከረም 19-25, 2016 ባለው ሳምንት
26 ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች አውጁ
እነዚህ ሁለት የጥናት ርዕሶች፣ ይሖዋ ካሳየን ጸጋ የምናገኛቸውን በርካታ ጥቅሞች ያብራራሉ። በተጨማሪም ይሖዋ ላሳየን ፍቅር ያለን አመስጋኝነት፣ ሌሎችም ከይሖዋ ጸጋ መጠቀም የሚችሉበትን መንገድ እንድንነግራቸው ሊያነሳሳን የሚገባው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።