የርዕስ ማውጫ
ከጥቅምት 24-30, 2016 ባለው ሳምንት
ከጥቅምት 31, 2016–ኅዳር 6, 2016 ባለው ሳምንት
8 የይሖዋን በረከት ለማግኘት መታገላችሁን ቀጥሉ
ተጽዕኖ ሲደርስብንና የሚያስጨንቁ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ከባድ ሸክም የተጫነን ያህል ሊሰማን እንዲሁም በምሳሌያዊ ሁኔታ እጃችን ሊዝል ይችላል። በእነዚህ ርዕሶች ላይ የይሖዋ ኃያል እጅ፣ ያጋጠመንን ሁኔታ በጽናት ለመወጣት የሚያስችለንን ብርታትና ድፍረት የሚሰጠን እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን። የይሖዋን በረከት ለማግኘት ‘መታገል’ ወይም መፋለም የምትችለው እንዴት እንደሆነም እናያለን።
14 በከፍተኛ ባለሥልጣናት ፊት ለምሥራቹ መሟገት
ከኅዳር 7-13, 2016 ባለው ሳምንት
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአምላክ አገልጋዮች አለባበሳቸውና አጋጌጣቸው ሥርዓታማ፣ ንጹሕና በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ይፈልጋሉ፤ በዚህ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ለማክበር ይጥራሉ። ታዲያ አለባበሳችሁ አምላክን የሚያስከብር እንዲሆን ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?
ከኅዳር 14-20, 2016 ባለው ሳምንት
ከኅዳር 21-27, 2016 ባለው ሳምንት
28 እናንት ወላጆች፣ ልጆቻችሁ እምነት እንዲያዳብሩ እርዷቸው
ወጣቶች የማመዛዘን ችሎታቸውን በመጠቀም እምነታቸውን ማጠናከርና በእምነታቸው ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት መመከት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ በእነዚህ ሁለት የጥናት ርዕሶች ላይ እንመለከታለን። በተጨማሪም ክርስቲያን ወላጆች፣ ልጆቻቸው በአምላክና በቃሉ ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ለመርዳት ሲጥሩ ትምህርቱን አስደሳች አድርገው ማቅረብ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ እናያለን።