የርዕስ ማውጫ
ከመስከረም 25, 2017–ጥቅምት 1, 2017 ባለው ሳምንት
ከጥቅምት 2-8, 2017 ባለው ሳምንት
8 “ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነው የአምላክ ሰላም”
የመጀመሪያው ርዕስ ይሖዋን በትዕግሥት ለመጠበቅ ፈቃደኞች መሆን ያለብን ለምን እንደሆነ ያብራራል። በተጨማሪም በጥንት ዘመን የኖሩ ታማኝ ወንዶችና ሴቶች የተዉት ምሳሌ በትዕግሥት መጠበቅ እንድንችል የሚረዳን እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን። ሁለተኛው ርዕስ ደግሞ ይሖዋ ጨርሶ ያልገመትነውን ነገር በማከናወን ያልተጠበቁ ነገሮችን የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ያብራራል። ይህን መመርመራችን በእሱ ላይ ያለንን እምነት እንድናጠናክርና ለእኛ ሲል እርምጃ የሚወስድበትን ጊዜ በትዕግሥት እንድንጠብቅ ይረዳናል።
13 የሕይወት ታሪክ—ፈተናዎችን በጽናት መቋቋም በረከት ያስገኛል
ከጥቅምት 9-15, 2017 ባለው ሳምንት
17 መጥፎ ልማዶችን ማስወገድና እንዳያገረሹብን መከላከል
ከጥቅምት 16-22, 2017 ባለው ሳምንት
22 አዲሱን ስብዕና መልበስና እንደለበስን መቀጠል
የመጀመሪያው ርዕስ አሮጌውን ስብዕና ገፎ መጣል ሲባል ምን ማለት እንደሆነና እንዲህ ማድረጋችን አጣዳፊ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራል። በተጨማሪም መጥፎ ልማዶች እንዳያገረሹብን መከላከል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል። በሁለተኛው ርዕስ ላይ ደግሞ የአዲሱ ስብዕና ክፍል የሆኑ አንዳንድ ባሕርያት የትኞቹ እንደሆኑና እነዚህን ባሕርያት በሕይወታችንና በአገልግሎታችን ማንጸባረቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።
30 ከታሪክ ማኅደራችን