የርዕስ ማውጫ
ከታኅሣሥ 25-31, 2017 ባለው ሳምንት
ከጥንት ዘመን ጀምሮ፣ መዝሙር የይሖዋ ሕዝቦች በሚያቀርቡት አምልኮ ውስጥ ትልቅ ቦታ ነበረው። ይሁንና አንዳንዶች፣ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ መዘመር ያሳፍራቸው ይሆናል። ከመዘመር ጋር በተያያዘ ያለብንን ፍርሃት አሸንፈን ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ማቅረብ የምንችለው እንዴት ነው? ይህ ርዕስ በደስታ ለመዘመር የሚያነሳሱንን ምክንያቶች እንዲሁም የመዘመር ችሎታችንን ለማሻሻል የሚረዱንን አንዳንድ ሐሳቦች ያብራራል።
ከጥር 1-7, 2018 ባለው ሳምንት
ከጥር 8-14, 2018 ባለው ሳምንት
በጥንቷ እስራኤል ውስጥ ከነበረው የመማጸኛ ከተሞች ዝግጅት ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንችላለን። የመጀመሪያው ርዕስ፣ በዛሬው ጊዜ ኃጢአት የፈጸሙ ሰዎች ይሖዋን መሸሸጊያ ማድረግ የሚችሉባቸውን መንገዶች ያብራራል። ሁለተኛው ርዕስ ደግሞ ይሖዋ የተወው ምሳሌ ሌሎችን ይቅር ለማለት፣ ለሕይወት አክብሮት ለማሳየትና ፍትሐዊ ለመሆን እንዴት እንደሚረዳን ያሳያል።
ከጥር 15-21, 2018 ባለው ሳምንት
ከጥር 22-28, 2018 ባለው ሳምንት
25 ማንኛውም ነገር ሽልማቱን እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ
እነዚህ ሁለት ርዕሶች ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት ለቆላስይስ ክርስቲያኖች በሰጠው ምክር ላይ የተመሠረቱ ናቸው። የመጀመሪያው ርዕስ፣ የብዙዎችን ትኩረት የሚስቡ ወይም አሳማኝ የሚመስሉ ዓለማዊ ሐሳቦችን ስንሰማ ምን ማድረግ እንዳለብን ያብራራል። ሁለተኛው ርዕስ ደግሞ ይሖዋ ቃል የገባልንን በረከቶች እንድናጣ ሊያደርጉን የሚችሉ ነገሮችን እንዴት ማስወገድ እንደምንችል ይገልጻል።