መግቢያ
የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ ይመጣል?
‘የወደፊቱ ጊዜ ለእኔና ለቤተሰቤ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?’ የሚለው ጥያቄ ያሳስብሃል? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦
“ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”—መዝሙር 37:29
ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ ለሰው ልጆችና ለምድር ምን ዓላማ እንዳለው ያብራራል። በተጨማሪም ከዚያ ዝግጅት ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለግክ ምን ማድረግ እንዳለብህ የሚጠቁም ሐሳብ ይዟል።