የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/93 ገጽ 3
  • “ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 2/93 ገጽ 3

“ማስታወቂያዎች

◼ በየካቲት የሚበረከቱ ጽሑፎች:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች እንቅስቃሴ መገምገም ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸውን ለማሟላት ችግር ያለባቸው የዘወትር አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎች አቅኚዎቹ እርዳታ የሚያገኙበትን ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ሐሳብ ለመስጠት እንድትችሉ ጥቅምት 1 ቀን 1992 እና ጥቅምት 1 ቀን 1991 የተላኩትን የማኅበሩን ደብዳቤዎች (S-201–AM) ከልሷቸው። በተጨማሪም 9–68 የመንግሥት አገልግሎታችን መጽሔት አባሪ (ጭማሪው ስለቀጠለ የአሠራር ደንቦችን ማቃለል ያስፈልጋል) አንቀጽ 12–20 ተመልከቱ።

◼ የመታሰቢያው በዓል ማክሰኞ ሚያዝያ 6 ቀን 1993 ይከበራል። ምንም እንኳን ንግግሩ ቀደም ብሎ ሊጀመር ቢችልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ግን ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ማዞር የማይገባ መሆኑን እባካችሁ አስታውሱ። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቀው በስንት ሰዓት ላይ እንደሆነ ለማወቅ በአካባቢው ካሉ ምንጮች አረጋግጡ። ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በስተቀር በዚያን ቀን ሌላ ስብሰባ አይኖርም። ጉባኤያችሁ ማክሰኞ ቀን ስብሰባ ያለው ከሆነና ክፍት የመንግሥት አዳራሽ የሚገኝ ከሆነ ስብሰባውን በሳምንት ውስጥ ለሌላ ቀን አዛውሩት። የአገልግሎት ስብሰባችሁ ከተነካ ለዚያ ሳምንት የተዘጋጀውን በተለይ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎችን በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ልታስገቡ ትችላላችሁ። የክልል የበላይ ተመልካች ጉብኝት ያላችሁ ጉባኤዎች ማክሰኞ ማታ የሚደረገውን የተለመደ ስብሰባ በሌላ ቀን ለማድረግ ዕቅድ ማውጣት ይኖርባችኋል።

◼ በመጋቢትና በሚያዝያ ረዳት አቅኚዎች ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች አሁንኑ ዕቅድ ማውጣትና ማመልከቻቸውን አስቀድመው መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊውን የመስክ አገልግሎት ዝግጅት እንዲያደርጉና በቂ ጽሑፍ እንዲኖር ለማድረግ እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

◼ በዚህ ዓመት በገለልተኛ ክልሎች ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚዎች በመሆን ለማገልገል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች በጉባኤያቸው የሽማግሌዎች አካል (ወይም የአገልግሎት ኮሚቴ) በኩል ሊያመለክቱ ይችላሉ። ሽማግሌዎችም ማመልከቻቸውንና የድጋፍ ደብዳቤያቸውን ግፋ ቢል እስከ ሚያዝያ 15, 1993 ድረስ መላክ አለባቸው።

◼ አንድን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ካነጋገራችሁ በኋላ ሁለት ጊዜ ያህል ካስጠናችሁትና ሰውየው ጥናቱን እንደሚቀጥል ለማመን የሚያስችል ምክንያት ካለ አዲስ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ብላችሁ ሪፖርት ልታደርጉት እንደምትችሉ አስታውሱ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ