መጠበቂያ ግንብ በተገቢው ጊዜ የሚቀርብ መንፈሳዊ ምግብ
1 ወደ 114 ለሚጠጉ ዓመታት ያህል መጠበቂያ ግንብ አንባቢዎቹ በመንፈሳዊ ንቁ ሆነው እንዲቀጥሉ ሲያስጠነቅቅ ቆይቷል። የመጠበቂያ ግንብ ጓደኛ የሆነው ንቁ! መጽሔትም ፈጣሪ በኛው ትውልድ ውስጥ ሰላማዊና ሥጋት የሌለበት አዲስ ዓለም እንደሚያመጣ በገባው ቃል ላይ ያለንን እምነት ይገነባል። እነዚህ ሁለት መጽሔቶች በአንድ ላይ በመሆን በጨለመው ዓለም ውስጥ መንገዳችንን የሚያበሩልን ቋሚ መሣሪያዎች ሆነው ቆይተዋል። (ኢሳ. 60:2) የአምላክ ቃል እውነት በፍጹም አይለወጥም፤ ሆኖም ይሖዋ እነዚህንና ሌሎች መሣሪያዎችን ተጠቅሞ መንፈሳዊውን ‘ምግብ በተገቢው ጊዜ’ ሲሰጠን የአምላክን ቃል በሚመለከት ያለን ማስተዋል ይበልጥ ግልጽ እየሆነ ይሄዳል። — ማቴ. 24:45፤ ምሳ. 4:18
2 መጽሔቶቹን በተሻለ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው፦ ሰዎች መጠበቂያ ግንብን እንዲሁም ንቁ! መጽሔቶችን እንዲያነቡ በጋለ የአድናቆት ስሜት በማበረታታት እየተቀበልን ላለነው መንፈሳዊ ማስተዋል አመስጋኝነታችንን ለማሳየት እንችላለን። በዚህ ወር ከቤት ወደ ቤት በምናደርገው ሥራ በመጀመሪያ ጉብኝታችን ላይ ወይም መደበኛ ያልሆነ ምስክርነት በምንሰጥበት ጊዜ ሰዎች ኮንትራት እንዲገቡ እንጋብዛለን። የመጽሔት ደንበኞቻችሁ ወይም መጽሔቶቻችንን ማንበብ ደስ እንደሚላቸው የምታውቋቸው ሰዎች ኮንትራት እንዲገቡ ጋብዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናቸው ሰዎች የራሳቸው ኮንትራት አላቸውን? ይህም ለመጽሔቶቹ ቋሚ የሆነ ኮንትራት የመግባታቸውን ጠቃሚነት እንዲገነዘቡት ልንረዳቸው የምንችልበት እጅግ በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው። ኮንትራት እንዲገቡ ያቀረባችሁላቸውን ግብዣ ካልተቀበሉ በቅርቡ የወጡትን እትሞች ከአንድ ብሮሹር ጋር አበርክቱላቸው።
3 ለሰዎች ዘላለማዊ ደኅንነት ያለን አሳቢነት ተስፋና ማጽናኛ በሚሰጠው የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት ረገድ ያላቸው ፍላጎት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ንቁዎች እንድንሆን ይገፋፋናል። እውነተኛ ፍላጎት እንዳላቸው እንዴት ለማወቅ ትችላላችሁ? በመጽሔት፣ በትራክት ወይም በብሮሹር ላይ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦች ስታወያዩት የቤቱ ባለቤት የሚያሳየውን ስሜት አስተውሉ። ልብ ብሎ ያዳምጣልን? መጽሐፍ ቅዱስን ይቀበላልን? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሚነበቡበት ጊዜ ይከታተላልን? ለምታቀርቡለት የአመለካከት ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይሰጣልን? እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ በአንድ ሳምንት ውስጥ ወይም አንድ ሳምንት ከመሙላቱ በፊት ተመልሳችሁ ለመጠየቅ ዝግጅት አድርጉለት፤ በዚያ ጊዜም ተጨማሪ ውይይት አድርጉ።
4 እያንዳንዱ የመጽሔቶቹ ዕትም ለሥራ ባልደረቦች፣ ለትምህርት ቤት ጓደኞችና ለዘመዶች ሊበረከት ይችላል። መጽሔቶቹን ዕቃ ለምንገዛቸው ነጋዴዎችና በመንገድ ላይ ምስክርነት በምንሰጥበት ጊዜ ልናበረክታቸው እንችላለን።
5 አዳዲስ መጽሔቶች ለጉባኤው እንደተላኩ በተቻለ ፍጥነት ለአስፋፊዎች እንዲደርሱ ሊደረግ ይገባል። አዲስ እትም ሲደርሳችሁ መጽሔቱን ከዳር እስከ ዳር አንብቡት። በአካባቢያችሁ ያሉትን ሰዎች በጣም የሚያሳስቧቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? የዓለም ሰላምና ደኅንነት? የኢኮኖሚው ጉዳይ? የመኖሪያ አካባቢ ሁኔታ? መጠበቂያ ግንብ ሰዎች ለችግሮች ሁሉ ብቸኛ መፍትሔ ወደሆነችው ወደ አምላክ መንግሥት ዘወር እንዲሉ ያደርጋል። (ዳን. 2:44፤ ማቴ. 6:10) በእውነትም ይህ “ከታላቁ አስተማሪያችን” የሚመጣ እጅግ ውድ የሆነ ስጦታ ነው። — ኢሳ. 30:20
6 ሚያዝያና ግንቦት በመስክ አገልግሎታችን ላይ የበለጠ ሰዓት እንድናውል የሚያስችሉን በጣም ጥሩ የሆኑ አጋጣሚዎች ይሰጡናል። ግንቦት አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ብዙዎች ለረዳት አቅኚነት ሊመዘገቡ ይችላሉ። ሁላችንም በእነዚህ ሁለት ወራት ውስጥ የመስክ አገልግሎታችንን ከፍ ለማድረግና የምናገኛቸውን ሁሉ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እንዲያነቡ በጋለ የአድናቆት ስሜት ለማበረታታት የግል ግቦች ማውጣት እንችላለን።