ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- በግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ኮንትራት ማስገባት። በሰኔ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። (እንግሊዝኛ) በሐምሌና በነሐሴ፦ ከሚከተሉት ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! ወይም የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች። መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S-14-AM) ላይ ሊጠይቁ ይችላሉ።
◼ ማኅበሩ ከ1986 እስከ 1991 የወጡት የእንግሊዝኛ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች (ባውንድ ቮልዩምስ) በማተም ላይ ሲሆን አቅርቦቱም ቋሚ ይሆናል። እነዚህን ጥራዞች ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጥያቄውን በጉባኤው በኩል መላክ ይችላል። በቀጣዮቹ ዓመታት የሚወጡትን የእንግሊዝኛ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች እንዲሁም የ1992 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዝ ቋሚ አቅርቦት ስለሚኖራቸው በማንኛውም ሰዓት ብትጠይቁ ልታገኟቸው ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ ጥራዞቹን (ባውንድ ቮልዩሞቹን) ማግኘት የሚቻለው በልዩ ትዕዛዝ እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።
◼ በኮምፒዩተር ዲስኬቶች ተቀርጸው የወጡ ሌሎች አዳዲስ የእንግሊዝኛ ጽሑፎች:- ባለ ማጣቀሻው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል። እነዚህ አዲስ የወጡ የኮምፒዩተር ዲስኬቶች የአዲሲቱ ዓለም ትርጉምን እና ማስተዋል የተባለውን መጽሐፍ ሁለት ጥራዞች አንድ ላይ የያዙ ናቸው። እነዚህ ዲስኬቶች የተዘጋጁት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ ሲሆን የሚገኙትም በ5 1/4–ኢንች 1.2–ሜጋባይት ወይም በ3 1/2–ኢንች 1.44–ሜጋባይት ዲስኬቶች ነው። በእነዚህ ዲስኬቶች ለመጠቀም ቢያንስ 18 ሜጋባይት የሚሆን ባዶ ቦታ ያለው ባለ ሃርድ ዲስክ ኮምፒዩተር ያስፈልጋል። ለጉባኤዎች ሁሉ የተላከው ደብዳቤ ስለነዚህ አዳዲስ ዕቃዎችና ዕቃዎቹን ለማግኘት ማዘዝ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የተቀረጸባቸውን ዲስኬቶች ወደፊትም ማግኘት ይቻላል።
◼ ማኅበሩ ሲዲ–ሮም (CD-ROM) የያዘ የኮምፒዩተር ዲስኬት እያዘጋጀ ነው። ሲዲ–ሮም ለማንበብ ብቻ የሚያስችል ሜሞሪ ያለው ኮምፓክት ዲስክ ነው። ይህ ዲስክ ከአዲሲቱ ዓለም ትርጉም፣ ማስተዋል ከተባለው መጽሐፍ ጥራዞች፣ ከ1950 እስከ 1993 ድረስ ካሉት መጠበቂያ ግንቦች እንዲሁም ሕጋዊ ባለመብት ከሆንንባቸው ከሌሎቹ በርካታ የማኅበሩ ጽሑፎች ውስጥ በማጣቀስ በኮምፒዩተር ስክሪን ላይ ለማየት ያስችላል። በተጨማሪም ሲዲ–ሮም በኮምፒዩተሩ ውስጥ ከእነዚህ ጽሑፎች ልዩ ልዩ ሐሳቦችን ለማፈላለግ የሚያስችል በማኅበሩ የተዘጋጀና እንደ ሁኔታው ሊለዋወጥ የሚችል ፕሮግራም የያዘ ነው። ሲዲ–ሮም የተባሉትን ዲስኬቶች ለማንበብ እንዲቻል ተስማሚ የሆነው መሣሪያ ያስፈልጋል። ይህን ሲዲ–ሮም የያዘ ዲስኬት ማግኘት የሚቻለው ከሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ በኋላ ይሆናል። እባካችሁ ስለ ዲስኬቶቹ መረጃ ለማግኘት ብላችሁ ለማኅበሩ አትጻፉ ወይም ስልክ አትደውሉ። ቴክኒክ ነክ የሆኑት መረጃዎች ተዘጋጅተው ሲያበቁ በአዲሱ ሲዲ–ሮም ለመጠቀም የሚያስፈልጉትን መሣሪያዎች ስለሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች የሚገልጽ ደብዳቤ ለሁሉም ጉባኤዎች እንልካለን።
◼ በ1994 የአገልግሎት ዓመት የምትጠቀሙባቸው ለአንድ ዓመት የሚያገለግሉ ቅጾች ለየጉባኤዎቹ ይላካሉ። እነዚህ ፎርሞች ሊባክኑ አይገባም። ልትጠቀሙባቸው የሚገባችሁ ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መሆን ይኖርበታል። በጥንቃቄ ከተጠቀማችሁባቸው የተላኩላችሁ ቅጾች ለአገልግሎቱ ዓመት በሙሉ ሊያገለግሏችሁ ይችላሉ። ስለዚህ በዓመቱ መሃል ለእነዚህ ቅጾች የሚሆን ተጨማሪ ማዘዣ መላክ አያስፈልጋችሁም። የሚላኩላችሁን ቅጾች ዝርዝር የሚያሳየውን የነሐሴ 14, 1992 ደብዳቤ ተመልከቱ። በዝርዝሩ ላይ የሌሉ ቅጾች እንዲላኩላችሁ ከፈለጋችሁ ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ ቀጥሎ ያሉት ጽሑፎች መታተማቸው አቁሟል:-
በእንግሊዝኛም በአማርኛም፦ ሕይወት ዓላማ አለው።
◼ ቀጥሎ ያሉትን አዳዲስ የብሬል ጽሑፎች ማዘዝ ይቻላል:-
በቀላል እንግሊዝኛ የተዘጋጁ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር — 1993 (በአራት ጥራዞች)፤ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት (በ1989 እንደገና ታርሞ የታተመ፤ በአምስት ጥራዞች)፣ የ1993 የቲኦክራቲካዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም (በአንድ ጥራዝ)፣ ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆን? (ትራክት ቁጥር 19፤ በአንድ ጥራዝ)፣ ለተጨነቁት የሚሆን መጽናኛ (ትራክት ቁጥር 20፤ በአንድ ጥራዝ)፣ በቤተሰብህ ኑሮ ተደሰት (ትራክት ቁጥር 21፤ በአንድ ጥራዝ)፣ በእርግጥ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? (ትራክት ቁጥር 22፤ በአንድ ጥራዝ)።
በብሬል የተዘጋጁ ጽሑፎችን ስታዝዙ ለብሬል ዴስክ ብላችሁ ጻፉበት። በብሬሉ ጽሑፍ የሚጠቀመውን ሰው ስምና አድራሻም ጨምራችሁ ጻፉ።
◼ የአምልኮ አንድነት የተባለው መጽሐፍ በመስክ ላይ የሚታደል የዘመቻ መጽሐፍ አለመሆኑን አስታውሱ። የማስጠኛ መጽሐፍ ነው።
◼ ጉባኤያችሁ የመንግሥት አዳራሽ ማሠሪያ ገንዘብ ካሁኑ መሰብሰብ ጀምሯልን? መዋጮውን አሁኑኑ ብትጀምሩ ጥሩ ነው።
◼ የመጽሔት ኮንትራት ዋጋ ማረሚያ:- ለጉባኤዎች በቅርቡ በተላከው የጽሑፎች ዋጋ መግለጫ ላይ ከውጭ አገር በአየር ስለሚላኩ መጽሔቶች ኮንትራት የተሰጠው ዋጋ እንደሚከተለው ታረሟል:- ለአንድ ዓመት የአንድ መጽሔት ኮንትራት ዋጋ ለአቅኚዎች 90 ብር፤ ለሌሎች 100 ብር ነው። በአንድ ጥቅልል ውስጥ 7 ቅጂዎች ለሚያስመጡ ለእያንዳንዱ አቅኚ 65 ብር ሲሆን ለእያንዳንዱ አስፋፊ 77 ብር ይሆናል።