የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/93 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 7/93 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፤ በሐምሌና በነሐሴ፦ ከሚከተሉት ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” ፣ በሥላሴ ማመን ይኖርብሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም ወይም የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች። በመስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። በጥቅምት፦ የንቁ! እና የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ኮንትራት ማስገባት ወይም የመጽሔቶቹን ነጠላ ቅጂ ማበርከት ይቻላል። ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን መጽሐፍ ጭምር ማበርከት ይቻላል። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት ወርሃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S-14-AM) ላይ መጠየቅ ይችላሉ። በጥቅምት ወር ለማበርከት የሚፈለገውን ያህል መጽሔት እዘዙ።

◼ ማኅበሩ ከ1980 እስከ 1985 የወጡትን የእንግሊዝኛ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች (ባውንድ ቮልዩምስ) በማተም ላይ ሲሆን በቋሚነት የሚቀመጡ ናቸው። እነዚህን ጥራዞች ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጥያቄውን በጉባኤው በኩል መላክ ይችላል። ይሁን እንጂ ጥራዞቹን (ባውንድ ቮልዩሞቹን) ማግኘት የሚቻለው በልዩ ትዕዛዞች እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።

◼ ትልልቅ ስብሰባዎችን ልዩ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል አንዳንድ አዳዲስ ጽሑፎች መውጣታቸው ነው። በተለያዩ ቦታዎች የስብሰባው ጊዜ ስለሚለያይ ጽሑፉን ቀደም ብለው የሚያገኙ ወንድሞች አሉ። እናንተም ይህን አጋጣሚ ብታገኙ የአካባቢው ስብሰባ እስኪደረግ ድረስ ጽሑፉን ለሌሎች እንዳታሳዩ ወይም ስለዚህ ጉዳይ እንዳታወሩ ትጠየቃላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ