የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/94 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 5/94 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ ኮንትራክት ማስገባት። ሰኔ፦ በማስታወቂያ ይነገራል። ከሐምሌ እስከ መስከረም፦ በጉባኤ ወይም በግል የሚገኙ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ የቆዩ መጻሕፍት እንደ ታላቁ አስተማሪ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዘላለማዊ ዓላማ፣ ሕይወት ይህ ብቻ ነውን?፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የሰው ልጅ መዳንና የሺህ ዓመት ግዛት የሚሉትን መጻሕፍት በ1 ብር ማበርከት ይቻላል። የየጉባኤዎቹ ጸሐፊዎች በአስፋፊዎች ወይም በአቅኚዎች ለተወሰዱት መጻሕፍት በቅጽ S-20-AM ላይ የዋጋው ልዩነት እንዲቀነስላቸው መጠየቁን መዘንጋት የለባቸውም። በተጨማሪም አረንጓዴ ቀለም ያለው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በ5 ብር ሊበረከት ይችላል። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ጊዜ በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S-14- AM) ላይ ማዘዝ ይችላሉ።

◼ የመንግሥት አዳራሽ ለመሥራት ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ሽማግሌዎች በአካባቢያቸው ከሚገኘው የአካባቢ የሕንፃ ሥራ ኮሚቴ ጋር መገናኘት ይኖርባቸዋል። የአካባቢ የሕንፃ ሥራ ኮሚቴዎች፣ ጉባኤዎች ጥበብ ያለበት ውሳኔ ማድረግ እንዲችሉ የሚረዷቸው አስፈላጊ መረጃዎች አሏቸው። አዳራሹ የሚሠራበት ሠፈር ወይም የቦታው ስፋት ምን ያህል መሆን እንዳለበት ወይም ግዢውን ሕጋዊ ማድረግን ወይም ለግንባታ የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች ወይም አስፈላጊውን የሰው ኃይል እንደመመደብ ያሉትን ትልልቅ ውሳኔዎች ከማድረጋችሁ በፊት የአካባቢ የሕንፃ ሥራ ኮሚቴዎች የሚሰጡትን ሐሳብ መስማት አርቆ አሳቢነት ነው። የአካባቢ የሕንፃ ሥራ ኮሚቴዎች የሕንፃውን ዲዛይን፣ ግንባታው እንዴት ቢሆን እንደሚሻልና የዋጋ ዝርዝርን በተመለከተ ሐሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

◼ ወንድሞችና እኅቶች፣ ልጆቻቸው እንዲሁም ጥናቶቻቸው ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 5:30 ወይም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 እስከ 10:30 ቅዳሜ ደግሞ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 5:30 ባሉት የሥራ ሰዓቶች በቦሌ የሚገኘውን ቤቴል ለግማሽ ሰዓት ያህል መጎብኘት ይችላሉ።

◼ የጽሑፍ አገልጋዩ በአስፋፊዎችና በአቅኚዎች የተወሰዱ ጽሑፎችን የሚቆጣጠርባቸው ሳምንታዊ የጽሑፍ መቆጣጠሪያ ቅጾች (S-61a- AM, S-61b-AM) አሉ። እነዚህንና ሌሎችንም አስፈላጊ ቅጾች ማዘዝ ይቻላል።

◼ ማንኛውም ጉባኤ የመንግሥት አዳራሽ ሲሠራ የገንዘብ ወጪውን የሚሸፍነው ጉባኤው ራሱን በመቻል ወይም በአካባቢ የሕንፃ ሥራ ኮሚቴ በኩል ብድር በመጠየቅ መሆን ይኖርበታል። ከሌሎች ጉባኤዎች ብድር ወይም እርዳታ ለመጠየቅ ደብዳቤ መጻፍ የለበትም።

◼ “አምላካዊ ፍርሃት” የተባለው የወረዳ ስብሰባ ጊዜያዊ ፕሮግራም:- በናይሮቢ (እንግሊዝኛ) ታኅሣሥ 23–25, 1994፣ በአዲስ አበባ ጥቅምት 21–23, 1994።

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ በእንግሊዝኛ:- አዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም bi-12፣ ትንሹ bi-25 (ጥቁር ወይም ቡና ዓይነት)፣ ትልቁ bi-8, ትንሹ የመዝሙር መጽሐፍ ፣ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ፣ የዮሐንስ ወንጌል በካሴት፣ 5 የተለያዩ ድራማዎች በካሴት እንዲሁም የ1970, 1971, 1972, 1973, 1974, 1980, 1981, 1982, 1984, 1985 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ