የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/94 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 7/94 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ ከሐምሌ እስከ መስከረም፦ በጉባኤ ወይም በግል የሚገኙ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ የቆዩ መጻሕፍት እንደ ታላቁ አስተማሪ እንዲሁም ዘላለማዊ ዓላማ፣ ሕይወት ይህ ብቻ ነውን?፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የሰው ልጅ መዳን እና የሺህ ዓመት ግዛት የተባሉትን የእንግሊዝኛ መጻሕፍት በ1 ብር ማበርከት ይቻላል። የየጉባኤዎቹ ጸሐፊዎች በአስፋፊዎች ወይም በአቅኚዎች ለተወሰዱት መጻሕፍት በቅጽ S-20-AM ላይ የዋጋው ልዩነት እንዲቀነስላቸው መጠየቁን መዘንጋት የለባቸውም። በተጨማሪም አረንጓዴ ቀለም ያለው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በ5 ብር ሊበረከት ይችላል። መስከረም፦ ከላይ የተገለጹት የቆዩ መጻሕፍት ካለቁ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ ልናበረክት እንችላለን። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ጊዜ በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S(d)-14)ላይ ማዘዝ ይችላሉ።

◼ ጸሐፊዎች S-20 የተባለው ቅጽ በሚጠይቀው መሠረት በቅጹ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች መፈረማቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ጸሐፊው ራሱ የS-20ን ቅጽ በሚያዘጋጅባቸው ጉባኤዎች ከ S-20ው ቅጽ በስተጀርባ የሁለት የተለያዩ ሰዎች ፊርማ ይሰፍር ዘንድ ከሱ በተጨማሪ ሌላ ወንድም ሊፈርም ይገባል።

◼ በትዕዛዝ ልታገኟቸው የምትችሏቸው ጽሑፎች፦ የ1994 የቀን መቁጠሪያ (በእንግሊዝኛ)፣ የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ (በእንግሊዝኛ)፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች (በአማርኛ)።

◼ ጽሑፍ ለሚታተምባቸው ቅርንጫፍ ቢሮዎች የሚላኩ ኮንትራቶችን እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ መሥራት ጀምረናል። የገባችኋቸው ኮንትራቶች ሳይደርሷችሁ ቀርተው ከተቸገራችሁ የላካችሁት የኮንትራት ማስገቢያ ቅጽ ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ እንድንችል ቀሪውን ቅጂ ላኩልን። በአየር የሚመጣ ኮንትራት፣ የኮንትራት ማስገቢያውን ቅጽ ከላካችሁ ቢበዛ ከሦስት ወር በኋላ በየብስ የሚመጣው ደግሞ ከአምስት ወር በኋላ ሊደርሳችሁ ይገባል። ሰዎችን በቀላሉ ኮንትራት ለማስገባት እንችል ዘንድ ኮንትራት የማስገቢያው ቅጽ በአማርኛ ተዘጋጅቷል። በየሦስት ወሩ የሚወጣውን የአማርኛ ንቁ! መጽሔት ግን ኮንትራት ማስገባት እንደማይቻል ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

◼ ሽማግሌዎች፣ ለጉባኤው የሚላኩ ደብዳቤዎች በሙሉ መነበብ እንዳለባቸው እባካችሁ አስታውሱ። ለምሳሌ በቅርቡ በ25/3/94 የተላከላችሁ በእንግሊዝኛ ስለሚደረጉ ስብሰባዎችና በአዲስ አበባ ስለሚኖሩ ፍላጎት ያላቸው የውጭ አገር ሰዎች የሚገልጸው ደብዳቤ እስካሁን ለጉባኤው ካልተነበበ ሊነበብ ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ