ማስታወቂያዎች
◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ይበረከታሉ። የመጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባትም ይቻላል። በኅዳር፦ ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት (በእንግሊዝኛ የወጣቶች ጥያቄ የተባለውን መጽሐፍ)። በታኅሣሥ፦ ራእይ መደምደሚያው። በጥር፦ ጉባኤው ያሉትን ከ1982 በፊት የታተሙ ማናቸውም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት። የቆዩ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች ማናቸውንም ብሮሹር ሊያበረክቱ ይችላሉ። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስከ አሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (s(d)AM-14) መጠየቅ አለባቸው። ከላይ የተጠቀሱት የቆዩ መጻሕፍት በብሩክሊን አይገኙም። የመጻሕፍቱ ዋጋ (1:00) በዚሁ ይቀጥላል። የሥነ ጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ ሞልታችሁ ልካችሁ ከሆነ የጉባኤው ሒሳብ ይስተካከላል።
◼ ከዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ጋር “የ1995 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ይላክላችኋል። ሲያስፈልጋችሁ እንድትጠቀሙበት በ1995 በሙሉ መቀመጥ አለበት።
◼ ጉባኤዎች ከጥቅምት የጽሑፍ ጥያቄያቸው ጋር ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር— 1995 የተባለውን ቡክሌት (በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጣልያንኛ፣ በትግርኛ) የ1995 የዓመት መጽሐፍንና የ1995 የቀን መቁጠሪያን (በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በጣልያንኛ) መጠየቅ መጀመር አለባቸው።
◼ ገንዘብ በፖስታ ሐዋላ በመጠቀም፣ በቼክ፣ (ለ“ይሖዋ ምሥክሮች” በማለት) በባንክ ሒሳባችን ላይ በማዛወር መላክ ወይም ቢሮአችን መጥቶ በካሽ መክፈል ይቻላል። ሽማግሌዎች የሒሳብ ቁጥሩን ሊጠይቁ ይችላሉ።
◼ አዲስ የመጡ ጽሑፎች፦ የ1993 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ጥራዞች (በእንግሊዝኛ)
◼ ተጨማሪ የ1994 የዓመት መጻሕፍት በእንግሊዝኛ መጥተውልናል። እነዚህንም ሆነ አሁን ያሉንን የ1994 ቀሪ የቀን መቁጠሪያዎች እንዲላክላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።