የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/94 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 12/94 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በታኅሣሥ፦ ራእይ መደምደሚያው። በጥር፦ ጉባኤው ያሉትን ከ1982 በፊት የታተሙ ማናቸውም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት። የቆዩ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች ታላቁ አስተማሪ (በአማርኛ) የተባለውን መጽሐፍ ሊያዙ ይችላሉ፤ ብሮሹሮችንም ማበርከት ይቻላል። በየካቲትና በመጋቢት፦ ለዘላለም መኖር ይበረከታል። ይህ መጽሐፍ ከተበረከተ በኋላ ተመላልሶ መጠየቅ ሊደረግ ይገባል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ጥረት መደረግ አለበት። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14) መጠየቅ አለባቸው።

◼ ለልዩ ስብሰባ ቀን የወጣ ፕሮግራም— አዲስ አበባ:- ጥር 7፣ 8፣ 14፣ 15፣ 21፣ 22፤ ሶዶ:- ጥር 7፤ ሻሸመኔና አለታ ወንዶ:- ጥር 8፤ ደሴና ባሕር ዳር:- ጥር 15፤ ነቀምት:- ጥር 22፤ ጅማ፣ ናዝሬትና ድሬዳዋ:- ጥር 29 1995።

◼ “ደስተኛ አወዳሾች” ለተሰኘው የ1995 የወረዳ ስብሰባ የወጣ ጊዜያዊ ፕሮግራም— አዋሳ:- ከመስከረም 15–17፤ አዲስ አበባ:- ከመስከረም 22–24 እና ከጥቅምት 6–8።

◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም እሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ ታኅሣሥ 1 ወይም በተቻለ መጠን ከዚያ ብዙም ሳይቆይ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ ጉባኤዎች በታኅሣሥ የጽሑፍ ትእዛዛቸው ላይ የ1994 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ጥራዞችን መጠየቅ መጀመር አለባቸው። እነዚህ ጽሑፎች ሲመጡ በተቻለ ፍጥነት እስክንልክላችሁ ድረስ ትእዛዙን “በጊዜያዊነት” እንይዘዋለን። ጥራዞች ልዩ ትእዛዞች ናቸው።

◼ ማኅበሩ ነሐሴ 1, 1993 ለሽማግሌዎች አካል የላከው ደብዳቤ ሕክምና ስለሚያስፈልገው ድንገተኛ ሁኔታ የሚናገሩት በኅዳር 1990 እና በመስከረም 1992 የወጡት የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ሁለት የመጽሔት አባሪ ክፍሎች እያንዳንዱ አዲስ ተጠማቂ ሊኖረው እንደሚገባ ይጠቁማል። ሽማግሌዎች ይህን መመሪያ ይከተላሉ። አስፈላጊ ከሆነ ፎቶ ኮፒ ሊደረጉ ይችላል።

◼ ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ጉባኤዎችና ቡድኖች ጽሑፎችን ቶሎ መላክ የሚቻልበትን መንገድ ለመፈለግ ከአዲስ አበባ ወዳላችሁበት ከተማ የሚመላለስ ዕቃዎችን የሚያጓጉዝ የንግድ ትራንስፖርት አገልግሎት ስለመኖሩ እንዲጠይቁ የጉባኤ ጸሐፊዎችን እንጠይቃለን። ከእነዚህ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ጋር እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የምንገናኝበትን አድራሻና የስልክ ቁጥር ማወቅ እንፈልጋለን።

◼ በአየር የሚላክ የአንድ ኮንትራት የተስተካከለ ዋጋ:- አማርኛ (መጠበቂያ ግንብ ብቻ) ወይም ጣልያንኛ— ለአስፋፊ:- ብር 96.50፤ ለአቅኚ 81 ብር፤ እንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ— ለአስፋፊ:- 112 ብር፤ ለአቅኚ ብር 96.50።

◼ አዲስ የመጡ ጽሑፎች:-

በአማርኛ፦ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የውይይት አርዕስት (ቡክሌት)፤ በሥላሴ ማመን ይኖርብሃልን? (ብሮሹር)፤ የሙታን መናፍስት (ብሮሹር)፤ ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን? (ትራክት–19)፤ ለተጨነቁ ሰዎች የሚሆን መጽናኛ (ትራክት–20)፤ በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት (ትራክት–21) ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? (ትራክት–22)። በኦሮምኛ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? (ትራክት–13)፤ የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ? (ትራክት–14)፤ ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት (ትራክት–15)፤ እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው? (ትራክት–16)።

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ጽሑፎች:-

በአማርኛ፦ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ፣ ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች (በተለይ ለቤተሰቦቻችንና ለልጆቻችን አስተማሪዎች ተብሎ የተዘጋጀ ብሮሹር።) በኦሮምኛ፦ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! በወላይትኛ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? (ትራክት–13)፤ የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ? (ትራክት–14)፤ ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት (ትራክት–15)፤ እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው? (ትራክት–16)።

◼ የመጡ ጽሑፎች:-

እንግሊዝኛ፦ የ1994 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ። ጣልያንኛ፦ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም፤ የአምላክ መንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች፤ ሕይወት እንዴት ተገኘ— በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት (ትንሹ)፤ ለዘላለም መኖር (ትንሹ)፤ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፤ የወጣቶች ጥያቄ፤ ማመራመር፤ የራእይ መደምደሚያው፤ ለይሖዋ የውደሴ መዝሙር ዘምሩ (ትንሹ)፤ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፤ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቁ ሰው፤ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ፤ እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት— እንዴት ልታገኝ ትችላለህ?፤ አምላክ ሰለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፤ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፤ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፤ “እነሆ!፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ”፤ በሥላሴ ማመን ይኖርብሃልን?፤ የሙታን መናፍስት— ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ጽሑፎች:-

አረብኛ፦ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፤ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ፤ አምላክ ሰለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፤ እንግሊዝኛ፦ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም፤ ባለ ማጣቀሻው መጽሐፍ ቅዱስ (ትልቁ)፤ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሺነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው ”፤ ደስታን ማግኘት የሚቻልበት መንገድ፤ የአምላክ መንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች፤ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፤ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት፤ ዋስትና ያለው ሕይወት ወደፊት እንዴት ልታገኝ ትችላለህ (ቡክሌት)፤ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፤ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፤ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፤ የይሖዋ ምሥክሮች በሃያኛው መቶ ዘመን (ብሮሹር)፤ ማንበብና መጻፍን ተማሩ፤ ችግሮቻችንን ለመፍታት ማን ያግዘን ይሆን? (ለሒንዱዎች የተዘገጀ ብሮሹር)፤ በሥላሴ ማመን ይኖርብሃልን?፤ የሙታን መናፍስት— ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፤ ገነትን የምታመጣው የአምላክ መንግሥት፤ ሕይወት ብዙ ሌላ ገጽታም አለው (ቡክሌት)፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?፤ ጦርነት የሌለበት ዓለም ይመጣ ይሆን? (ለአይሁዶች የተዘጋጀ ብሮሹር)፤ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች (1960፣ 1961፣ 1963፣ 1964)፤ የ1995 የቀን መቁጠሪያ።

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ካሴቶች:-

እንግሊዝኛ፦ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች አልበም— ጥራዝ 2 ከ1 ሳሙኤል እስከ መዝሙር ያሉት፤ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍትን የያዙ ነጠላ ካሴቶች። የድራማ ካሴቶች:- ከይሖዋ በመራቅ እምነታችሁን እንዳታጠፉ ተጠንቀቁ፤ ይሖዋ ስሙን የሚጠሩትን ያድናቸዋል፤ ሕግ አፍራሽ በሆነ ሕዝብ ላይ ይሖዋ የወሰነው ፍርድ፤ የይሖዋ ስም በመላዋ ምድር ይታወጃል፤ በረሃብ ዘመን ሕይወትን ማትረፍ።

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ የቪዲዮ ካሴቶች:-

እንግሊዝኛ፦ ፐርፕል ትሪያንግልስ (PAL)፤ ከስሙ በስተጀርባ ያለ ድርጅት (PAL)።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ