የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/96 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 2/96 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- የካቲት፦ የራእይ መደምደሚያ አለዚያም የቤተሰብ ኑሮ እና ወጣትነትህ እያንዳንዳቸው በ3 ብር። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት እንዲገቡ ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል። ማሳሰቢያ፦ እባካችሁ የሚያስፈልጋችሁን ጽሑፍ አሁኑኑ እዘዙ።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች እንቅስቃሴ መገምገም አለባቸው። የሚፈለግባቸውን ሰዓት ማሟላት ያስቸገራቸው ካሉ ሽማግሌዎች እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። በ9-68 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 ከ12-20 ባሉት አንቀጾች ውስጥ የቀረቡትን ነጥቦች ከልሱ።

◼ የመታሰቢያው በዓል ማክሰኞ ሚያዝያ 2, 1996 ይከበራል። ምንም እንኳ ንግግሩ ቀደም ብሎ ሊጀመር ቢችልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር እንደሌለበት እባካችሁ አስታውሱ። ፀሐይ የምትጠልቅበትን ሰዓት በአካባቢያችሁ ካሉ ምንጮች ጠይቃችሁ አረጋግጡ። በዚህ ዕለት ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በስተቀር ሌሎች ስብሰባዎች አይደረጉም። ጉባኤያችሁ ዘወትር ማክሰኞ ስብሰባ ካለው ስብሰባውን በሳምንቱ ውስጥ የመንግሥት አዳራሹ ነፃ በሚሆንበት ሌላ ቀን ልታደርጉት ትችላላችሁ። አዳዲስ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ መገኘት እንዳያስቸግራቸው በጣም አምሽታችሁ መጀመር የለባችሁም። በተጨማሪም ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ወይም ካለቀ በኋላ በበዓሉ ላይ የተገኙትን እንግዶች ሰላም ለማለት፣ ለአንዳንዶቹ ቋሚ መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ለማድረግ ወይም እርስ በርስ ለመበረታታት ጊዜ እስኪጠፋ ድረስ ፕሮግራሙ የተጣበበ መሆን የለበትም።

◼ በ1997 የሚደረገው የመታሰቢያ በዓል እሑድ መጋቢት 23, 1997 ይከበራል።

◼ በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ከአሁኑ ዕቅድ ማውጣትና ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊውን የመስክ አገልግሎት ዝግጅት እንዲያደርጉ ከማስቻሉም በተጨማሪ በቂ መጽሔቶችንና ሌሎች ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል።

◼ በወር ሁለት ጊዜ የሚወጣውን የትግርኛ መጠበቂያ ግንብ ኮንትራት መግባትና የሚበረከት ቅጂ ማዘዝ ይቻላል።

◼ ከአሁን በኋላ በኢጣሊያ የሚገኘው ቅርንጫፍ ከሌሎች ቋንቋዎች በተጨማሪ የእንግሊዝኛና የፈረንሳይኛ መጽሔቶች ኮንትራት ይልካል። ይህ ለውጥ የተደረገው ከስፔይን የሚመጣው የመጽሔት ኮንትራት በፖስታ አገልግሎት ረገድ አንዳንድ ችግሮች እንዳሉት ስላሳወቃችሁን ነው። ለውጡ ችግሩን እንደሚያስተካክለው ተስፋ አለን፤ ሆኖም ኮንትራት ያላችሁ ሁሉ የተደረገው ለውጥ መሥራት እስኪጀምር እንድትታገሱ እንጠይቃችኋለን። ኮንትራት ያለው ማንኛውም ሰው ከመጋቢት አጋማሽ በኋላ ባለው ጊዜም ችግር የሚያጋጥመው ከሆነ ስሙን፣ የኮንትራቱን ቀን፣ የትኛው መጽሔትና ቋንቋ እንደሆነ ገልጾ እንደገና ይጻፍልን።

◼ የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ወር ላይ የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር እሑድ ሚያዝያ 21 ይቀርባል። ንግግሩ “በጠማማ ትውልድ ውስጥ ያለ ነቀፋ መኖር” የሚል ርዕስ ይኖረዋል። በዚህ ቀን የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤያችሁን የሚጎበኝ ከሆነ ልዩ ንግግሩ ከዚያ ቀጥሎ ባለው ሳምንት ይሰጣል።

◼ ከመጋቢት ጀምሮ በወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚቀርበው አዲሱ የሕዝብ ንግግር “በክርስቶስ አመራር ሥር ያለ ታማኝ ጉባኤ” የሚል ይሆናል።

◼ በአንዳንድ ሁኔታዎች የተነሳ ከአሁን ጀምሮ ቤቴልን መጎብኘት የሚችሉት አስፋፊዎችና ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑ ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።

◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ነገሮች:- ቱ ዚ ኤንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ የተባለው የቪዲዮ ካሴት፤ ፕላስቲክ የባጅ መያዣ (ብር 0.50)፤ ፕላስቲክ የአገልግሎት ክልል ካርድ መያዣ (ብር 0.50)።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ