የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/96 ገጽ 1
  • ጊዜው ተለውጧል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጊዜው ተለውጧል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልናውጀው የሚገባ መልእክት
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • መንግሥቱን ስበኩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ሃይማኖት
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ‘መልካም ዜና ማብሰር’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 4/96 ገጽ 1

ጊዜው ተለውጧል

1 መጽሐፍ ቅዱስ ‘የዚች ዓለም መልክ ተለዋዋጭ ነው’ ይለናል። (1 ቆሮ. 7:31) ይህ አባባል ለጊዜያችን ምንኛ ተስማሚ ነው! በእኛ ዕድሜ እንኳ በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ፈጣን የሆነ የአስተሳሰብና የጠባይ ለውጥ አይተናል። ለእነዚህ ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት ተቀባይነት ባለው ሁኔታ ለማቅረብ ከፈለግን አቀራረባችን ከተለዋዋጩ ጊዜ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆን አለበት። ምሥራቹን ሰዎችን በሚያስደስትና ልባቸውን በሚነካ መንገድ ማቅረብ እንፈልጋለን።

2 ከብዙ ዓመታት በፊት አብዛኞቹ ሰዎች የተረጋጋ ሕይወት ስለነበራቸውና ደህንነት ይሰማቸው ስለነበር በብዙ አገሮች ውስጥ የሚካሄደው የይሖዋ ምሥክሮች ሥራ ከአሁኑ የተለየ መልክ ነበረው። ሃይማኖት በሰዎች ሕይወት ውስጥ የተቀደሰ ቦታ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ከፍ ተደርጎ ይታይ ነበር። በዚያን ጊዜ የምሥክርነቱ ሥራ በአብዛኛው የሚያተኩረው በመሠረታዊ ትምህርቶች ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሐሳቦችን በማፍረስ ላይ ነበር። ዛሬ የሰዎች ሕይወት በሁከት ተሞልቷል። ሃይማኖት አክብሮት አጥቷል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ጥቂቶች ናቸው። በተጨማሪም የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ብዙዎች በአምላክ ላይ የነበራቸውን እምነት አሳጥቷቸዋል።

3 አንድ ተጓዥ የበላይ ተመልካች “በአሁኑ ጊዜ የሰዎች ሕይወት በብዙ ችግሮችና ውጣ ውረዶች የተሞላ ስለሆነ ሰዎች እነዚህን ሁኔታዎች እንዴት መወጣት እንደሚችሉ ማስተማር አለብን” ብሏል። በአሁኑ ጊዜ ሰዎች በአብዛኛው የሚጨነቁት ስለ ራሳቸው፣ ስለ ቤተሰባቸውና፣ ስለሚያስፈልጓቸው ነገሮች ነው። ሰዎች ሲገናኙ ብዙውን ጊዜ የሚያወሩት ስለ እነዚህ ነገሮች ነው። በምሥክርነቱ ሥራችን ይህንን በአእምሯችን መያዝ ያስፈልገናል።

4 አስተማማኝ ተስፋ የሚያቀርብልን የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው፦ አብዛኞቹ ሰዎች በሰብዓዊ መንግሥታት ላይ ትምክህት የላቸውም። በሕይወት ዘመናቸው የተሻለ ጊዜ የሚመጣ መስሎ አይታያቸውም። የሐሰት ሃይማኖት ምንም ዓይነት ተስፋ ሊሰጣቸው አልቻለም። የሰው ዘር የአምላክን መንግሥት ምሥራች መስማቱ በጣም አስፈላጊ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው። የአምላክ መንግሥት በሰው ዘር ፊት ለተደቀኑት ችግሮች መፍትሔ የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ አስረዷቸው።

5 እምነት የሚጣልበት ብቸኛው መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፦ በዛሬው ጊዜ በሰው ጥበብና በዓለማዊ ፍልስፍና የሚተማመኑ መሪዎች አብዛኛውን ሕዝብ በተሳሳተ አቅጣጫ መርተውታል። ሰዎች ‘የሰው ልጅ አካሄዱን ማቅናት እንደማይችል’ አልተገነዘቡም። (ኤር. 10:23 አዓት) ሰዎች ‘በሙሉ ልባቸው በይሖዋ መታመንና በራሳቸው ማስተዋል መደገፍ’ እንደሌለባቸው ሊማሩ ይችላሉ፤ ይህም ሊማሩ ከሚችሏቸው ነገሮች ሁሉ የበለጠ ዋጋ ያለው ነገር ነው። (ምሳሌ 3:5) ጊዜው ቢለወጥም መጽሐፍ ቅዱስ አልተለወጠም። ስለዚህ በአገልግሎታችን ላይ ሁልጊዜ የአምላክን ቃል በማጉላትና ሰዎች በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉትን መለኮታዊ መመሪያዎች እንዲያደንቁ ማስተማር ይኖርብናል። (2 ጢሞ. 3:16, 17) ሰዎችን ስናነጋግር ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ፣ ጥያቄዎቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመን በመመለስ እንዲሁም መጽሐፉን የማጥናትንና የያዘውን ተግባራዊ እውቀት በተግባር የማዋሉን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ በማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ጠቃሚ መሆኑን ማሳየት አለብን።

6 ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ ብንኖርም እንኳ የአገልግሎታችን ዋነኛ ዓላማ አልተለወጠም። የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ፣ ሰዎች በአምላክ ቃል ላይ እምነት እንዲገነቡ ማድረግና ሌሎች ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ የማጥናቱን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ መርዳት ይኖርብናል። የምንናገረው ነገር የምንመሰክርላቸው ሰዎች በጊዜው ከሚያስፈልጋቸው ነገር ጋር የሚስማማ መሆን አለበት። እንዲህ እያደረግን ከሌሎች ጋር የምሥራቹ ተካፋይ በመሆን ብዙ ሰዎችን ለመጥቀም እንችላለን።— 1 ቆሮ. 9:19, 23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ