ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ፦ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” (በእንግሊዝኛ)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሙታን መናፍስት ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ) እና የምትወዱት ሰው ሲሞት። መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ነጠላ ቅጂዎች እና ኮንትራት ማስገባት። ኅዳር፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ ለተበረከተላቸው ሰዎች ክትትል ለማድረግ ልዩ ጥረት ይደረጋል።
◼ ለ1997 የአገልግሎት ዓመት የሚያገለግሉ በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ እየተላኩ ነው። እባካችሁ እነዚህን ቅጾች ሳታባክኑ ተጠቀሙባቸው። ቅጾቹ ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ ሊውሉ ይገባል። ተጨማሪ ወይም ሌላ ዓይነት ቅጽ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ በሚቀጥለው ጊዜ በምትልኩት S-14-AM (የጽሑፍ ማዘዣ) ቅጽ ላይ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።
◼ እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ መቁጠሪያ ቅጾች (S(d)-18-AM) ይደርሱታል። የጉባኤው ጸሐፊና የጽሑፍ አገልጋዩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች የሚቆጠሩበትን ቀን ለመወሰን በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ተገናኝተው መነጋገር አለባቸው። በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች ሁሉ አንድ በአንድ መቆጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ ላይ መሞላት አለበት። በጉባኤው እጅ ያሉትን የመጽሔቶች ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ከመስከረም 6 በፊት ዋናውን ቅጂ ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ በፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው ቆጠራው ትክክል መሆኑን መቆጣጠር ያለበት ሲሆን ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ደግሞ ተሠርቶ ያለቀውን ቅጽ መመርመር ይኖርበታል። ጸሐፊውና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በቅጹ ላይ ይፈርማሉ።