ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ የተበረከተላቸውን ሰዎች ሁሉ ተከታትሎ ለመርዳት ልዩ ጥረት ይደረጋል። ታኅሣሥ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ። ጥር፦ በጉባኤ ያሉ ከ1984 በፊት የታተሙ 192 ገጽ ያላቸው መጽሐፎች። እነዚህ ጽሑፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት ወይም የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች አድርገው የተሰኙትን መጽሐፎች ማበርከት ይችላሉ። በተጨማሪም ሁሉም ወንድሞች ጎድስ ኢተርናል ፐርፐዝ፣ ኢዝ ዚስ ላይፍ ኦል ዜር ኢዝ፣ ማንስ ሳልቬሽን የተሰኙት መጽሐፎች በጉባኤያቸው ውስጥ ካሉ አበርክተው እንዲጨርሱ እናበረታታለን። በጉባኤ ውስጥ የሚገኙትን እነዚህን ቅጂዎች ለማበርከት እርስ በእርሳችን ልንረዳዳ እንችላለን። የካቲት፦ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም በጉባኤ ያሉ 192 ገጽ ያላቸው ሌሎች መጽሐፎችንም ማበርከት ይቻላል።
◼ የመንግሥት ዜና ቁ. 34 የተሰኘው ትራክት ያላችሁ ጉባኤዎች አስፋፊዎች ከቤት ወደ ቤትም ሆነ በሌላ መንገድ ሌሎቹን መደበኛ ትራክቶች በሚያበረክቱበት መንገድ ይህንንም ትራክት እንዲያበረክቱ ልታበረታቱ ትችላላችሁ። አስፋፊዎች አመቺ ከሆነ ቤታቸው ሄደው ላላገኟቸው የቤት ባለቤቶች አንድ ቅጂ ትተው ሊሄዱ ይችላሉ። ይህንንም ሲያደርጉ በመንገዱ የሚተላለፉ ሰዎች ማየት በማይችሉበት መንገድ ማድረግ አለባቸው። ውድ የሆነ መልእክት የያዘውን ይህን ትራክት በሰዎች እጅ ለማስገባት ጥረት መደረግ ይኖርበታል።
◼ አንዳንድ ጊዜ አንድ ዓይነት የሆኑ ሁለት የመጽሔት ኮንትራት ማስገቢያ ቅፆች ይደርሱናል። በዚህ ምክንያት የሚፈጠረውን ችግር ለማስወገድ እንዲቻል በሁለት የተለያዩ ቅጾች ላይ አንድ ዓይነት ቋንቋ ያላቸውን ተመሳሳይ መጽሔቶች መሙላት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ሁለት የተለያዩ ስሞችን እንዲጠቀም ሐሳብ እናቀርባለን።
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ (ትንሹ እትም)፣ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፤ እንግሊዝኛ፦ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፤ ፈረንሳይኛ፦ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፤ ትግርኛ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ (ትንሹ እትም)፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?