የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/97 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 4/97 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሚያዝያ፦ በወሩ ውስጥ ባሉት ቅዳሜዎች የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች፤ እንዲሁም በሌሎቹ ቀናት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘው ብሮሹር። ግንቦት፣ ሰኔና ሐምሌ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ትኩረት ይደረጋል። ነሐሴ እና መስከረም፦ ከሚከተሉት 32 ገጽ ካላቸው ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም በአንድ ብር ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?​—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ)፣ የሙታን መናፍስት​—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? እና ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም።

◼ ጉባኤ የሚሰበሰቡ ሁሉ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት አዲስ ኮንትራት ለማስገባት ወይም ለማሳደስ እንዲሁም ለራሳቸው የግል ኮንትራት መግባት የሚኖርባቸው በጉባኤው በኩል ነው።

◼ በአገልግሎት ለምታገኟቸው ሰዎች የቅርንጫፍ ቢሮውን ስልክ ቁጥር ከመስጠታችሁ በፊት ሁኔታውን በጥንቃቄና በማስተዋል እንድታስቡበት እናበረታታችኋለን። ያለን የስልክ መስመር አንድ ብቻ ከመሆኑም በላይ ጥሪ ይበዛበታል፤ እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች የሚደውሉት ቁሳዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ ሲሉ ብቻ ነው። ስለዚህ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በምታገኙበት ጊዜ ሁሉ እባካችሁ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ማኅበሩ እንዲደውሉ አታድርጉ። የስብከቱ ሥራ ተልእኳችን አንዱ ዘርፍ በሆነው ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ዝግጅት በማድረግ ራሳችሁ በግል እርዳታ አድርጉላቸው። ፍላጎት ያሳየው ግለሰብ በሌላ ክልል የሚገኝ ከሆነ ለእኛ እንዲያሳውቀንና አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንድንችል እባካችሁ የጉባኤያችሁን ጸሐፊ አነጋግሩ። በተጨማሪም ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ የሌላቸው ወይም ራቅ ባለ አካባቢ የሚኖሩ ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን በምታናግሩበት ጊዜ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንዲችሉ የፖስታ ሣጥን ቁጥራችንን ንገሯቸው። የስልክ ቁጥራችንን መስጠት አስፈላጊ የሚሆንባቸው አንዳንድ ምክንያቶች ይኖሩ ይሆናል። ሆኖም ብዙዎቹ ቢጽፉልን እንመርጣለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ