የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/97 ገጽ 1
  • የታመኑ መሆን ይክሳል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የታመኑ መሆን ይክሳል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ይሖዋ ከልብ ለሚፈልጉት ወሮታ ከፋይ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • አገልግሎታችንን ለማስፋት ጥረት እናድርግ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • በሁሉም ነገር ታማኝ ናችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 7/97 ገጽ 1

የታመኑ መሆን ይክሳል

1 ዕብራውያን 11:6 [NW] አምላክ “ከልባቸው የሚፈልጉትን እንደሚክስ” ይነግረናል። ለእርሱ ያደሩትን ‘በጥቂቱ የታመኑ’ አገልጋዮቹን ከሚክስበት መንገድ አንዱ ‘በብዙ ነገሮች ላይ መሾም’ ነው። (ማቴ. 25:23) በሌላ አባባል ብዙውን ጊዜ ይሖዋ የተከናወነውን ጥሩ ሥራ የሚክሰው ለታመኑ ምሥክሮቹ ተጨማሪ የአገልግሎት መብቶችን በመስጠት ነው።

2 ሐዋርያው ጳውሎስ የታመነ ሆኖ በመገኘቱ በአውሮፓና በትንሿ እስያ ባሉ ከተሞችና መንደሮች የማገልገል መብት በማግኘት ተክሷል። (1 ጢሞ. 1:12) ምንም እንኳን ጳውሎስ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም ትልቅ ጥረት ቢጠይቅበትም ለተቀበለው መብት ከፍተኛ አድናቆት ነበረው። (ሮሜ 11:13፣ ቆላ. 1:25) ለመስበክ የሚያስችሉትን አጋጣሚዎች በመፈለግ ከልብ የመነጨ አድናቆቱን አሳይቷል። ቅንዓት በተሞላው እንቅስቃሴው አማካኝነት እምነቱን በተግባር ገልጿል። የእርሱ አርአያነት ያሉንን የአገልግሎት መብቶች ከፍ አድርገን እንድንመለከታቸው ያደርገናል።

3 ይሖዋ አገልግሎት ሰጥቶናል፦ ጳውሎስ ለተካሰበት ተጨማሪ የአገልግሎት መብት የነበረውን ዓይነት አመለካከት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? በአገልግሎት ያለንን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የምንችልባቸውን መንገዶች እንፈልጋለን። መደበኛ ባልሆነ መንገድም ሆነ ከቤት ወደ ቤት ለመስበክ የሚያስችሉንን አጋጣሚዎች በሙሉ እንጠቀምባቸዋለን። በቤታቸው ያላገኘናቸውን ሰዎች በሌላ ጊዜ ለማግኘት እንጥራለን እንዲሁም ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ ተመልሰን እንጠይቃለን። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት የያዝነውንም ቀጠሮ እናከብራለን።

4 ጳውሎስ አገልግሎታችንን ‘በጥድፊያ ስሜት እንድናከናውን’ አሳስቧል። (2 ጢሞ. 4:2 NW) አጣዳፊ የሆነ ነገር አፋጣኝ ትኩረትን ይሻል። በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ በመስጠት አገልግሎታችንን በጥድፊያ ስሜት እናከናውናለንን? ለምሳሌ ያህል በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ላይ ለመስክ አገልግሎት ልንመድበው የሚገባንን ጊዜ መዝናኛዎች ወይም ሌሎች የግል ጉዳዮች እንዲያስተጓጉልብን አንፈልግም። የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ በፍጥነት እየቀረበ መሆኑን ስለምናምን ልንሠራቸው ከምንችላቸው ሥራዎች ሁሉ ይበልጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነው የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ እንደሆነ እንገነዘባለን።

5 ለአምላክ የታመን መሆናችንን የምናሳየው ለእሱ እውነተኞችና ታማኞች በመሆንና እንድናከናውነው የሰጠንን ሥራ ዘወትር በመፈጸም ነው። ይሖዋ የታመን ሆነን በመገኘታችን በእጅጉ ይክሰን ዘንድ አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ እንፈጽም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ